የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠም GPS እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 24, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጨ-4/2018ዓ.ም

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ በመደበኛ በጀት ተሸከርካሪዎች ላይ የሚገጠም GPS እቃ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

1. በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው

3. የግዥው መጠን ብር ከ200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

4. ጨረታው አዲስ ዘመን ጋዜጣ በአየር ላይ ከዋለበት ቀናት ጀምሮ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውን የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

6. የግዥ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /Specification/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡ ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 13/15 የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /BID BOND/ ለሚወዳደሩበት ግዥ ዓይነት ጠቅላላ ዋጋ ተሽከርካሪዎች ላይ የሚገጠም GPS እቃ 50,000/ሀምሳ ሺህ ብር/ እቃ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ/CPO/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡ በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በቢሮ ህጋዊ ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ማቅረብ አለባቸው፡፡

8. የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ ጋር ተያይዞ በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሉትን የግዥ ዓይነት በመጥቀስ ግልጽ ጨረታ የሚል ተፅፎበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት እና በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን መግባት ይኖርበታል፡፡

9. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአብክመ ትምህርት ቢሮ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ክፍል ጨረታው ይከፈታል፡፡

10. የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

11. የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ስትመጡ በቢሮው አካውንት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቁጥር 1000012857253 ወይም አባይ ባንክ ቁጥር 2012116113625016 ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ደረሰኙን ፎቶ ኮፒ በመያዝ የጨረታ ሰነድ የምትወስዱ ይሆናል፡፡

12. ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ አብክመ ትምህርት ቢሮ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ በፋክስ ቁጥር 058 222 0814 በመላክ ወይም በስልክ ቁጥር 058-2-26-62-67/ 058-3-20-39-99 በመደወል ማግኘት ይቻላል፡፡

13. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *