Your cart is currently empty!
የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ እና በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልጽ ጨረታ በማወዳደር አሸናፊ በመለየት ዓመታዊ ውል ይዞ መግዛት/ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ እና በስሩ ላሉ ሴክተር መ/ቤቶች በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች የጋራጅ ጥገና የነዳጅ እና ቅባት የጎሚስታ ጥገና አገልግሎት ለማግኘት፡–
- ሎት1 ቀላል መኪናዎች መለዋወጫ፣
- ሎት 2. ከባድ መኪናዎች መለዋወጫ፣
- ሎት 3. ቢሾፍቱ የከተማ አውቶብስ፣
- ሎት 4. የመኪና ጎማና ባትሪ፣
- ሎት5. የከባድ መኪናዎች የጋራጅ ጥገና
- ሎት 6 የቀላል መኪናዎች የጋራጅ ጥገና፣
- ሎት 7 የጎሚስታ ጥገና፣
- ሎት 8- የነዳጅ እና ቅባት በግልጽ ጨረታ በማወዳደር አሸናፊ በመለየት ዓመታዊ ውል ይዞ መግዛት ይፈልጋል፤
ስለዚህ ከዚህ ባታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትወዳደሩ ተጋብዛችኋል።
1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላችሁ፣
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላችሁ እና የብቃት ማረጋገጫ ወረቀት ማቅረብ የሚችል
3. ግዥው ከ200000 ብር በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመውሰድ ሲመጡ ከላይ ከ1 እስከ 3 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎችን ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ሰነድ ይዘው መቅረብ አለባቸው
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በብር 200 ብር ከግዥ ፋይናስ አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 18 ላይ በመምጣት ከ13/1/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 27/1/2018 ዓ.ም 11፡30 ድረስ ደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥ ፋይናስ ቡድን አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ላይ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
6. የሚገዙ እና የሚሰሩት አይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ። የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝና ፍሉድ መደረግ የለበትም
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሞሉትን ድምር 2% ከባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ወይም በሁኔታው ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው እንዲሁም አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ያሸነፉበትን ዋጋ 10% የውለታ ማስከበሪያ ማስያዝ አለበት
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም ወጥ በሆነ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በመሙላት በፖስታ በማሸግ ደሴ ከተማ አስ/ር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥና ፋይናንስ ቡድን አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ላይ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ 28/1/2018 ዓ.ም 3፡30 ድረስ ሰነዱን በማስገባት ይታሸጋል።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት 28/1/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት ላይ ደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ በግዥ አዲሱ ቢሮ 3ኛ ፎቅ ላይ ይከፈታል።
10. የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይሆናል።
11. ውድድሩ የሚካሄደው በጥቅል ድምር ወይም በሎት ድምር ውጤት ነው፡፡
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ስለጨረታው ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስ.ቁ 033 312 0617 ደውለው መረዳት ይችላሉ።
የደሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ