Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት አላቂ ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 25, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን የግዥና ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት አላቂ ዕቃዎችን፣ ቋሚ ዕቃዎችን እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ሎት 1 አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች
- ሎት 2 ህትመት አገልግሎት
- ሎት 3 የጋራዥ አገልግሎት ግዥ ለመኪኖች የሰርቪስ አገልግሎት
- ሎት 4 ሌሎች አላቂ እቃዎች
- ሎት 5 የውሃና የቆሎ መስተንግዶ አገልግሎት
- ሎት 6 የጽዳት እቃዎች
- ሎት 7 የደንብ ልብስ
- የባለ 8 ባለ 5 ኮከብ የሆቴል የመስተንግዶ አገልግሎት
- ሎት 9 የኤሌክትሮኒክስ እቃ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡–
1. ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ
2. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ
4. የአቅራቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው፣
5. የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /Tin No / ያላቸው፣
6. በመንግሥት ግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ–ገጽ (WWW.PPA.gov.et)
7. ተጫራቾች የሚያሲዙት የጨረታ ማስከበሪያ/CPO
- ሀ. ሎት 1 አላቂ የጽሕፈት መሣሪያዎች………….10,000 ብር
- ለ. ሎት 2 የህትመት ስራዎች…………………………10,000 ብር
- ሐ. ሎት 3 የጋራዥ አገልግሎት የመኪና ጥገና……….10,000 ብር
- መ. ሎት 4. ሌሎች አላቂ እቃዎች…………………………..5,000 ብር
- ሰ. ሎት 5. የውሃና የቆሎ መስተንግዶ አገልግሎት…….5,000 ብር
- ረ. ሎት 6 የጽዳት እቃዎች………………………………….5,000 ብር
- ሸ. ሎት 7 የደንብ ልብስ………………………………….5,000 ብር
- ቀ. ሎት 8 ባለ 5 ኮከብ ሆቴል አገልግሎት……………………….10,000 ብር
- በ ሎት 9 የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች …………………….. 20,000 ብር
8. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባችሁ ነገር ግን CPO ያላስያዘ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፣
9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ዕቃ ናሙና መቅረብ አለበት እስፔስፍኬሽን ለሚያስፈልጋቸው ደግሞ በተረጋገጠ መንገድ ሞልተው ያስገቡ።
10.ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 15ኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብና የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት 200 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፣
11. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፣
12. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፣
13.ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒውን ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል ለየብቻ በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁን ማህተምና ፊርማ የተወዳደራችሁበትን የሎት አይነት በፖስታው ላይ እየጻፋችሁ አስገቡ ካልጻፋችሁበት ደግሞ ፖስታችሁ እንደማይከፈት እያወቃችሁ የተባሉትን በሙሉ በማድረግ በግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወደ ህንጻው ስትገቡ በቀኝ በኩል ባለው ሊፍት 15ኛ ፎቅ ፊት ለፊት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ
14.ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ
ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፤
ለ. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ፣
15.ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትከክል መሙላት አለባቸው
16. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፣ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታ ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከ8 የሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፣
17.ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ 3፡30 ይከፈታል። ነገር ግን 11ኛ ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡–
1. ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ ይህ ካልሆነ ግን መ/ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል።
2. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡–አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለሥልጣን ክፍለ ከተማ፣ አራዳ ወረዳ፣ 1 ፒያሳ እስታትስቲክስ ጎን ዋስትና ንግድ ማእከል እናት ህንጻ ፊት ለፊት 15 ፎቅ ላይ ይገኛል።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-12768-25 ይደውሉ።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን