Your cart is currently empty!
የአንድነት ፓርክ የመኪና መቆሚያ ህንጻ (ፓላስ ፓርኪንግ) ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሱቅ መሸጫ የሚሆን ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 22, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የአንድ ፓርክ የመኪና መቆሚያ ህንጻ(ፓላስ ፓርኪንግ) ግልጽ የወጣ ለቢሮ ወይም ስሱቅ አገልግሎት የሚውል ኪራይ ጨረታ ቁጥር 3/2018
የአንድነት ፓርክ የመኪና መቆሚያ ህንጻ (ፓላስ ፓርኪንግ) ለቢሮ አገልግሎት ወይም ለሱቅ መሽጫ የሚሆን ክፍሎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች።
1. በዘርፉ ህጋዊና የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላችውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. ተጫራቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡበት ከጨረታ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው ሰነድ ቅደም ተከተል መሰረት ቫትን ጨምሮ ነው።
3. ተጫራቾች የቦታውን ግምት በካሬ በተቀመጠው የመነሻ ዋጋን ተንተርሶ የሚቀርብ ይሆናል።
4. ተጫራቾች የሚያሸንፉበትን ቦታ ላይ ለሽያጭ የሚቀርቡበትን ዕቃና አገልግሎት ዋጋ እንዲሁም የድርጅታቸውን ሙሉ ፕሮፋይል ሞልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. እያንዳንዱ ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲፒኦ ወይም የባንክ ጋራንቲ በጽ/ቤቱ ስም ማሲያዝ ይኖርበታል።
6. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በጽ/ቤቱ እንግዳ መቀበያ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
7. እያንዳንዱ ተጫራች ቴክኒካል እና ፋይናሻል ዶክመንት በተለያ ፓስታ ታሽጎ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. እያንዳንዱ ተጫራች ከተሰማሩበት ንግድ ሥራ ዘርፍ ውጪ በሆነ ንግድ ፍቃድ መወዳደር አይችሉም።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8:00 ተዘግቶ በዕለቱ ከሰዓት 8:15 ሰዓት ይከፈታል።
10. ፓርኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር +251 11-154-3103 /+251 11 857 8718 ፋክስ ቁጥር 226292
የአንድነት ፓርክ የመኪና መቆሚያ ህንጻ (ፓላስ ፓርኪንግ)