Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓትን ተከትሎ ለኤሌክትሪካል እና መካኒካል ወ/ሾፕ የሚውሉ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 25, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤስ/ፍፋግ/ግጨ-005/2018
ተቋማችን የኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓትን ተከትሎ ለኤሌክትሪካል እና መካኒካል ወ/ሾፕ የሚውሉ ግብዓቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
| ተ.ቁ | የዕቃው ዓይነት | የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) | የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት | የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት | 
| 1 | ለኤሌክትሪካል እና መካኒካል ወ/ሾፕ የሚውሉ ግብዓቶች ግዥ | 500,000.00 (አምስት መቶ ሺ) | መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት | መስከረም 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት | 
- ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የታደሰ የታክስ ከሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
- ተቋማችን አሌክትሮኒከስ ግዥ ሥርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ስለጀመረ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩትን ሰነዶች በመያዝ ወደ ተቋማችን ቢሮ ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ከፍል በአካል በመቅረብ መለያ ስም እና የሚስጥር ቁጥር ለመውሰድ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚስጥር ቁጥራቸውን ከወሰዱ በኋላ ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ባንክ የከፈሉበትን የከፍያ ሰነዱን ስካን በማድረግ misrakfan@gmail.com ወይም getv3010@gmail.com በሚል ኢሜይል አድራሻ መላክ ይኖርባቸዋል።
- በመቀጠል በተቋሙ የዌብሳይት አድራሻ https://eeusrmvendorportal.ethiopianelectricutility.et/irj/portal ላይ በተሰጣቸው መለያ ስም እና የሚስጥር ቁጥር በመግባት ማግኘት ይችላሉ።
- የኤሌክትሮኒክስ የጨረታ ሰነድ ያገኘ ተጫራች የኤሌክትሮኒክስ ዘዴን በመጠቀም ምላሽ ለመስጠት ተቋማችን በሚያመቻቸው የስልጠና training orientation/ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ስልጠናውን በመውሰድ መሆን ይኖርበታል።
- አድራሻ፡- ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ከፍል ስልክ ቁጥር 011 26 6605/ 011 156-0148
- ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና <> በሚል መሆን ይኖርበታል !
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን የኤሌክትሮኒከስ ግዢ የምላሽ አሰጣጥ ስርአትን በመከተል ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት መሆን ይኖርባቸዋል፣
- ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን 8፡30 ሰዓት ላይ የኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርአትን በመከተል በኦንላይን ስለሚሆን በተራ ቁጥር 4 በተገለጸው መሰረት በኦን ላይን ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ኦሪጅናል እና ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎችናሙናውን ጨረታው በሚዘጋበት ቀንና ሰዓት ንብ ባንከ 10ኛ ፎቅ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ከፍል በአካል ማቅረብ አለባቸው።
- ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት