ተስፋ ድርጅት ሰርገኛ ጤፍ አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Reporter(Sep 28, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጤፍ ጨረታ ማስታወቂያ

ተስፋ ድርጅት በሲቨል ማህበራት ኤጄንሲ የተመዘገበ ህጋዊ ድርጅት ሲሆን በአገራችን በተለያዩ ክልሎች ማለትም በጋምቤላ፤ ቤንሻንጉል፣ በኦሮሚያ፣ በአማራና ሲዳማ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ባሉት ቅርንጫፎች በትምህርት፤ በሙያ ሥልጠና እና በተለያዩ የልማት ሥራዎች የኢኮኖሚ አቅማቸው ዝቅተኛ ለሆኑ ወገኖች አገልግሎት ይሰጣል:: ስለሆነም ለሚረዳቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ በታች የተገለፀውን የጤፍ አይነት አቅራቢዎችን በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::

..

አይነት

መለኪያ

ብዛት

ማስረከቢያ ቦታ

1

ሰርገኛ ጤፍ

ኩንታል

200

ተስፋ ድርጅት ደሴ ቅርንጫፍ

 

ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል::

1. የታደሰ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው መሆን አለባቸው::

2. በዘርፉ የየታደሰ የንግድ ፈቃድ እንዲሁም ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርቲፊኬት ያላቸው መሆን አለባቸው::

3. የግብር መለያ ቁጥር (in No) ሰርቲፊኬት ያለው::

4. ተጫራቾች የሚያስገቧቸውን የዋጋ ሰነዶች የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶኩመንት ለየብቻ ወይም ሁለቱን የታሸጉ ፖስታዎች በአንድ ፓስታ በማሸግ ከነሳምፕሉ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ መስከረም 29 ቀን 2018 .. ከቀኑ 600 ድረስ ተስፋ ድርጅት ዋናው መሥሪያ ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል::

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (አምሣ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ብቻ በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከቴክኒካል ዶኩመንቱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል::

6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት መስከረም 29 ቀን 2018 .. ከቀኑ 8.00 ሰዓት ይከፈታል::

7. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ፎርም ከድርጅቱ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመግዛት በተዘጋጀው ፎርም ብቻ ዋጋ ማስገባት ይኖርባቸዋል::

8. ተጫራጮቾች የሚያቅረቡት ዋጋ እስከ ማስረኪቢያ ቦታ ያለውን የትራንስፓርት ዋጋ ጭምር የያዘ መሆን አለበት::

9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::

አድራሻ፡

ተስፋ ድርጅት ዋናው /ቤት

አየር ጤና ሳሚ ካፌ ፊት ለፊት

ስልክ ቁጥር 0118 72 38 19

አዲስ አበባ

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *