የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት በዋናው መ/ቤት የሰራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን የካፍቴሪያ አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 27, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት

ለድርጅቱ በዋናው /ቤት የሰራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን የካፍቴሪያ አገልግሎት ግዥ ግልጽ ጨረታ ቁጥር EMPDE/NCB/05/2018 የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻና ማከፋፈያ ድርጅት በዋናው /ቤት ለሚያገለግሉ ሰራተኞች ለቁጥር 1 እና ለቁጥር 2 የካፍቴሪያ አገልግሎት ለመስጠት ፍላጎት ያላቸው ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች አወዳድሮ ለማከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም፣

1. ከምግብ ጋር ግንኙነት ያለው በዘርፉ ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ እና ግብር ከፋይ ሰርተፊኬት (TIN) ያለው፡፡

2. ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልጸውን ሰነድ የማይመለስ ብር 600 / ስድስት መቶ ብር/ በመክፈል ከትም/መሳሪ/ማም/ማከ/ድርጅት ዘወትር በሥራ ሰዓት ጠዋት 200 ሰዓት እስከ 630 ሰዓት እንዲሁም 730 ሰዓት እስከ 1030 ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 35 መውሰድ ይችለሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለቁጥር 1 እና ለቁጥር 2 የካፍቴሪያዎች የጨረታ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በሲፒኦ ወይም በባንክ ጋራንቲ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

4. ጨረታው መስከረም 27 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ በዚሁ እለት ከቀኑ 800 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ይከፈታል፡፡

5. ከላይ የተዘረዘሩትንና በጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተመለከቱትን ግደታዎች የምታሟሉ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ ትችላላችሁ።

6. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የድርጅቱ አድራሻ፡ከመገናኛ ወደ ጉርድ ሾላ በሚወስደው መንገድ ከሆሊ ሲቲ ሴንተር ህንጻ ሲደርሱ ወደ ቀኝ ታጥፎ ይገኛል፡፡

ለበለጠ መረጃ Tel/ 0116 463 481 መረጃ ማግኘት ይቻላሉ፡፡

የትምህርት መሳሪያዎች ማምረቻ እና ማከፋፈያ ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *