Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የተለያዩ 40 ካውንት እና ካውንት መነን ክር እንዲሁም ፓልም የምግብ ዘይት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Reporter(Sep 28, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የተለያዩ 40 ካውንት እና ካውንት መነን ክር
እንዲሁም ፓልም የምግብ ዘይት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
(የጨረታ ቁጥር ኢኢግልድ 004/2018)
1. የጨረታ ማስታወቂያ፡
ድርጅታችን ጥራት ያለው 40 ካውንት እና 60 ካውንት መነን ክር ምርት እንዲሁም ፓልም የምግብ ዘይት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፤ የዘመኑን ግብር ስለመከፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሠርፍትኬት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች አስፈላጊውን ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለሁሉም ምርቶች በጨረታው ላይ በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ።
- ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ ፊት ለፊት ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡30 እንዲሁም አርብ ከጠዋቱ 2፡00-5፡30 ከሰዓት ከ7፡30 – 11፡00 ሰዓት መወስድ ይችላሉ።
- በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ስም የተዘጋጀ ለ40 እና 60 ካውንት መነን ክር ምርት የብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እንዲሁም ለፓልም የምግብ ዘይት የብር 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ (በCPO) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ለብቻው በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- የጨረታ ማወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሰነዶች ጋር በታሸገ ኢንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማቅረብ ይችላሉ።
- ጨረታው በተመሳሳይ ቀን መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113-69-22-43/0113-69-18-86