የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር ዘይት ባለ 5 ሊትር፤ መኮረኒ፤ ሩዝ፤ ምስር ክክ፤ የተከካ የሽሮ እህል (አተር)፤ ጤፍ እና የተለያዩ አትክልቶችን ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 28, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ 
የጨረታ መለያ ቁጥር ADA/54/25

የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ፤ ከዚህ በታች የተጠቀሱትን፡ ዘይት ባለ 5 ሊትር ፡ መኮረኒ ፤ ሩዝ ፤ ምስር ክክ ፤ የተከካ የሽሮ እህል ( አተር ) ጤፍ እና የተለያዩ አትክልቶችን ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ በሥራ ሰዓት በመገኘት አዲስ አበባ ወሎ ሰፈር በኢትዮ ቻይና መንገድ ወንጌላዊት ሕንፃ አለፍ ብሎ ካስ ታወር ሕንፃ አጠገብ የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተከርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ በሚገኘው 3ኛ ፎቅ 308 ቢሯችን ድረስ በመቅረብ የጨረታ ሰነድ ከግዥ ከፍል መግዛት ይችላል ፡፡

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው፡-

  • የታደሰ የንግድ ፍቃድ ፤ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN)
  • የጨረታ ማስከበሪያ በድርጅታችን “የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር” ስም በአዋሽ ባንክ ወይም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ 20,000 /ሃያ ሺ ብር/ ሲ.ፒ.ኦ አሠርተው ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ፋይናንሻል ዶክመንት በፖስታ አሽገው መቅረብ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100 ብር (አንድ መቶ ብር) በመከፈል ሰነዱን ከኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር ግዥ ክፍል ዘወትር በሥራ ሰዓት ማግኘት ይችላሉ፡፡
  • የጨረታ ሰነዱ ላይ የድርጅቱ ክብ ማህተምና ፊርማ ማድረግ እንዲሁም ስርዝ ድልዝ ቢያጋጥም በፊርማ መረጋገጥ ይኖርበታል ፡፡
  • ድርጅታችን የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ፡፡
  • የጨረታው አሸናፊ የሆኑት ዕቃውን በአንድ ሳምንት ውስጥ ማቅረብ አለባቸው ፡፡
  • ለሽሮ እህል እና ለምስር ክክ ሩብ ኪሎ ሳምፕል ማቅረብ ግዴታ አለባቸው ፡፡
  • ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አርብ ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ይሆናል፡፡
  • ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ፡- 0949 231 127 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል ፡፡
  • ማሳሰቢያ፦ አትክልት ያሸነፈው ድርጅት በየ15 ቀኑ ለ2 ወራት ያለምንም ዋጋ ለውጥ ገፈርሳ ጉጂ ( ኬላ ) እና ቡራዩ በሚገኘው የምገባ ማእከላችን አትክልቱን ማቅረብ ይኖርበታል፡፡

የኢትዮጵያ ጉባዔ እግዚአብሔር ቤተክርስቲያን የእርዳታና ልማት ማህበር መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *