የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የአይ ሲ.ቲ መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Sep 28, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 003/2018

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት 2018 በጀት ዓመት ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች እና የአይ . መለዋወጫ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ

  • በዘርፉ ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  • የንግድ ምዝገባ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
  • የቫት ሰርተፍኬት
  • በመንገስት ገዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ

ሎት1. ቋሚ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች (ዴስክቶፕ ኮምፒዩተር፣ ሰርቨር እና ስዊች ግዥ)

ሎት2. አላቂ የአይሲቲ ዕቃዎች ከላይ በዝርዝር በቀረበው መሰረት በጨረታው መሳተፍ የሚሹ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የሚችሉ ሲሆን ለጥቃቅንና አነስተኛ ተቋማት ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የድጋፍ ደብዳቤ የጨረታ ሰነዱን በነጻ እንዲወስዱ ያስችላቸዋል። የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ ለሎት1 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ለሎት 2. 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) በሲ..ኦ፣ ቢድ ቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 15 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል ጉልህ  በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን ሎት በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን፤ የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒክ ዋና ሰነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት። ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም። ጨረታው በ16ኛው የስራ ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 430 በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም። የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።

  • ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ፡አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *