በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Reporter(Oct 01, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁስ

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ከዚህ በታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ የተመለከቱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢ ድርጅቶች በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

የሚፈለጉት ኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን አይነትና ብዛት

ተ.ቁ

የእቃው አይነት

መለኪያ

ብዛት

1

ተንቀሳቃሽ ስልክ (Galaxy Samsung A16, 128 GB, 8 RAM 8, 5th Generation

ቁጥር

8

2

ኮምፒዩተር (Hp laptop Computer Core i5, 15.6 inch, 8 GB RAM, SSD 512, 12th Generation

ቁጥር

6

3

ኮምፒዩተር (HP laptop Computer Core i7, 14 inch, 1TB SSD, 16 GB RAM, 13th Generation.

ቁጥር

1

4

ዴስክ ቶፕ ኮምፒዩተር (Dell Desktop computer Core i3)

ቁጥር

1

5

ፕሪንተር (HP printer With scanner, HP Leaser MFP 135W)

ቁጥር

2

ስለሆነም የተዘረዘሩትን የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶችን አይነትና ብዛት ማቅረብ የምትችሉ እንዲሁም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች

የምታሟሉ አቅራቢዎች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን::

1. ከዚህ በፊት የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች አቅርቦት ላይ ሰርተው የሚያውቁ ለዚህም ካቀረቡላቸው ድርጅቶች የጽሁፍ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ

2. 2017 . የታደሰ የንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው

3. የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ወይም ቲን ተመዝጋቢ የሆኑ፣

4. ከላይ በተራቁ 1-3 የተዘረዘሩት መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የሚወዳደሩበትን ጠቅላላ ዋጋ ህጋዊ በሆነ የድርጅታቸው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ (ፕሮፎርማ) በማስፈር በድርጅታቸው ማህተምና ፊርማ አረጋግጠው በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ አዲስ አባባ በሚገኘው የኮሚሽናችን /ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::

5. ጨረታው በአስረኛው ቀን ከረፋዱ 400 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚያው ቀን ከረፋዱ 430 ላይ በፈለጉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። 10 ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል::

6. ኮሚሽኑ በተጫራቾች የቀረበውን ጨረታ ሰነድ ላይ የሰፈሩትን የቴክኒክና የፋይናንስ ዝርዝሮችን ከገመገመ በኋላ የጨረታው አሸናፊ የሆነውን ድርጅት ያሳውቃል:

7. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ከኮሚሽኑ ጋር በሚያደረገው የውል ስምምነት መሠረት ጨረታውን ማሸነፉ በተነገረው 5 ቀናት ውስጥ የኤልክትሮኒስ ቁሳቁሶችን ትክክለኛነት እና በአግባቡ መሰራታቸውን በኮሚሽናችን ባለሞያዎች ፍተሻ ካስደረገ በኋ ማስረከብ ቁሳቁሶችን የኮሚሽኑ ዋና /ቤት ድረስ አጓጉዞ ይጠበቅበታል::

8. የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ቁሳቁሶቹን አቅርቦ ለኮሚሽኑ እንዳስረከበ 5ቀናት ውስጥ ክፍያ ይፈጸምለታል::

9. ኮሚሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብት አለው

አድራሻ፡ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት

በኢ///ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን /ቤት

ለተጨማሪ ማብራሪያ . 0910006953/0912122895

አዲስ አበባ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *