Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ጥራት ያለው 40 ካውንት እና 60 ካውንት መነን ክር ምርት እንዲሁም ፓልም የምግብ ዘይት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Reporter(Oct 01, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የተለያዩ 40 ካውንት እና 60 ካውንት መነን ክር እንዲሁም ፓልም የምግብ ዘይት ግዥ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
(የጨረታ ቁጥር ኢኢግልድ 004/2018)
1. የጨረታ ማስታወቂያ፡
ድርጅታችን ጥራት ያለው 40 ካውንት እና 60 ካውንት መነን ክር ምርት እንዲሁም ፓልም የምግብ ዘይት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው የሚያረጋግጥ ክሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ፣ የግብር ከፋይነት ሠርፍትኬት፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ያላቸው መሆን ይጠበቅባቸዋል።
2. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች አስፈላጊውን ህጋዊ ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ተጫራቾች ለሁሉም ምርቶች በጨረታው ላይ በሙሉም ሆነ በከፊል መጫረት ይችላሉ።
4. ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ፒያሳ ከሊፋ ህንፃ ፊት ለፊት ቢስ መብራት ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ ሐሙስ ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡30 እንዲሁም አርብ ከጠዋቱ 2፡00-5፡30 ከሰዓት ከ7፡30 – 11፡00 ሰዓት መወስድ ይችላሉ።
5. በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ስም የተዘጋጀ ለ40 እና 60 ካውንት መነን ክር ምርት የብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እንዲሁም ለፓልም የምግብ ዘይት የብር 1,500,000 (አንድ ሚሊዮን አምስት መቶ ሺህ ብር) በሲፒኦ (በCPO) ብቻ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት ለብቻው በታሸገ ኢንቮሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
6. የጨረታ ማወዳደሪያ ዋጋቸውን ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሰነዶች ጋር በታሸገ ኢንቮሎፕ አንድ ኦርጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ስዓት ድረስ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ማቅረብ ይችላሉ።
7. ጨረታው በተመሳሳይ ቀን መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም ለማህበረሰቡ ይጠቅማሉ ያላቸውን ውሳኔዎች የመወሰን መብቱ የተጠበቀ ነው:: ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0113-69-22-43/ 0113-69-18-86