በልደታ ክ/ከተማ ትም/ፅ/ቤት በወረዳ 10 ስር የሚገኘው የፍሬህይወት ቁ.1 ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሚፈልጋቸውን የትምህርት ቁሳቁሶችና ሌሎች ግብዓቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Lessan(Oct 11, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልጽ የጨረታ ማስታወቅያ

የግዥ መለያ ቁጥር 01/2018 ዓ.ም

በልደታ ክ/ከተማ ትም/ፅ/ቤት በወረዳ 10 ስር የሚገኘው የፍሬህይወት ቁ.1 ቅድመ አንደኛ አንደኛና መካከለኛ /ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የሚፈልጋቸውን የትምህርት ቁሳቁሶችና ሌሎች ግብዓቶችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚሁም መሰረት፦ 

  • ሎት 1 የደንብ ልብስ ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 16,500.00
  • ሎት 2 የደንብ ልብስ ስፌት የጨረታ ማስከበሪያ 3,000.00
  • ሎት 3 የፅህፈት መሣርያና አላቂ የቢሮ ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 16,500.00
  • ሎት 4 ህትመት የጨረታ ማስከበሪያ 1,950.00
  • ሎት 5 ለአላቂ የህክምና ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 363.00
  • ሎት 6 ለአላቂ የትምህርት ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 2,513.00
  • ሎት 7 አላቂ የፅዳት ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 18,000.00
  • ሎት 8, ልዩ ልዩ መሳሪያዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 375.00
  • ሎት 9. ለፕላንት ማሽነሪ ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 1500.00
  • ሎት 10 ለፕላንት ማሽነሪ ዕቃዎች ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ 1500.00
  • ሎት 11 ለህንፃ ቁሳቁስ ተገጣጣሚ ጥገና የጨረታ ማስከበሪያ 1500.00
  • ሎት 12 ለፕላንት ማሽነሪ ቋሚ ዕቃዎች በር የጨረታ ማስከበሪያ 4,500.00
  • ሎት 13 ለህንፃ ቁሳቁስ ቋሚ ዕቃዎች ግዢ የጨረታ ማስከበሪያ 3,000.00

መስሪያ ቤቱ ባወጣው ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ። በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ላላቸው ተጫራጮች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ በመንግስን አስ ኤጀንሲ ድረ ገጽ በአቅራቢዎች ምዝገባ ዝርዝር የተመዘገቡ የተንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

  1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበርያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ በተወዳደሩበት ሎት የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በትምህርት ቤቱ ስም በማሰራት ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  2. የጨረታ አሸናፊ 10% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል።
  3. ተጫራቾች በአዲስ ልሳን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ በተከታታይ አስር የስራ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በፍሬህይወት ቁ,1 ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 7 በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላል።
  4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቅያው ከወጣበት ዕለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፍሬህይወት ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፡ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት ሁለተኛው ጊቢ ፋይናንስ ቢሮ በረንዳ ላይ ለጨረታ በተዘጋጀው ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  5. ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከቀኑ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዛኑ ቀን ከቀኑ 4፡30 ሰዓት የፍሬህይወት ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደት ቤት ይከፈታል የመከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሣጥኑ ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩባቸውን ሎት 1፣ ሎት 3፣ ሎት 4፣ ሎት 5፣ ሎት 6፣ ሎት 7፣ ሎት 8 እና ሎት 9 ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ናሙና ማቅረብ የማይችሏቸውን ቋሚ ዕቃዎችን ሎት 12 እና ሎት 13 በፎቶ ግራፍ የተደገፈ ናሙና (በስፔሲፊኬሽን መሰረት) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ት/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
  8. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ለእያንዳንዱ ሻት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።
  9. የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም።
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች በራሣቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈፃሚው መሥሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  12. ት/ቤቱ ዕቃዎችን የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አድራሻ፡- በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ሜክሲኮ የፍሬህይወት ቁ.1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት በመከላከያ ኢንጅነሪንግ (ሜቴክ) ገባ ብሎ ሌጆ አልሙኒየም አጠገብ ነው
  • ስልክ 011 515 7818 ወይም 011 558 3860 የፍሬህይወት ቁı ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደ/ት/ቤት

በአዲስ አበባ አስተዳደር ት/ቢሮ በልደታ ክ/ከተማ ትም/ጽ/ቤት

የፍሬህይወት ቁ. 1 ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት