Your cart is currently empty!
የአቃቂ ቤዝክ ሚታልስ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ኬሚካሎችን (Furan Resin, Ferro Manganese, Zirko fluid/ISOMOI, Tin Metal 99.99%, Ramming Cement Tycore 245, Catalyst & Concret Cement For Ladle Lining) በአገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 12, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ቁጥር፣ አቤሜ ኢ/ሰቼማ /ግጨ/2018/01
የአቃቂ ቤዝክ ሚታልስ ኢንዱስትሪ የተለያዩ ኬሚካሎችን (Furan Resin, Ferro Manganese, Zirko fluid/ISOMOI, Tin Metal 99.99%, Ramming Cement Tycore 245,Catalyst&Concret Cement For Ladle Lining) በአገር ውስጥ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
- በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የግብር መክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ቅጂ፣ አግባብ ያለው በዘርፋ የታደሰ ንግድ ስራ ፍቃድ ቀጂውን፣ የንግድ ምዝገባ መስክር መረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት እና የግብር መክፈያ መለያ ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በአቃቂ ቤዝክ ሜታል ኢንዱስትሪ ስም ሒሳብ ቁጥር 1000014630906 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ–አርብ ጠዋት 2፡30_6፡00 ሰዓት ከሰአት 7፡:30–10፡30 ሰዓት ኢንዱስትሪያችን ቅጥር ግቢ በመቅረብ ሰነዱን ከግዥ ክፍል መግዛት ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺ ብር) በCPO ወይም bank guarantee ወይም Cash ቢያንስ ለ88 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ጨረታው በጋዜጣ ከታተመበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ኛ ወለል ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 22 ውስጥ ይከፈታል።
- ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
- ኢንዱስትሪው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ ሆኖ በኤንቨሎፕ አሽጐ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት፤
አድራሻ፡– ከአ/አ ወደ ዱከም መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ሸገር ከተማ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ ቁጥር 0114340409/0114350608
በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩኘ የአቃቂ ቤዝክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ