Your cart is currently empty!
የገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ የተሸከርካሪ መኪና እና ሞተር ሳይክሎች መለዋወጫ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 12, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ሁለተኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
የገቢዎች ሚኒስቴር ሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት
- የተለያዩ የተሸከርካሪ መኪና እና
- ሞተር ሳይክሎች መለዋወጫ ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው፣ በመንግስት ግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ ላይ የተመዘገቡ፣ ጨረታ ለመሳተፍ ማስረጃ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና እንዲሁም የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ዝርዝር መግለጫ (ስፔሲፊኬሽን) እና የተጫራቾች መመሪያ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000013485236 በማስገባት አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 46 በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 500.00 ከባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ቀን አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራች በሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አራተኛ ፎቅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ይከፈታል።
- የጨረታው ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከ11ኛው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ላይ የሚውል ከሆነ በቀጣዩ ቀን ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋ ቴክኒካል ዋናውንና አንድ ኮፒ እና ፋይናንሻል ዋነውንና አንድ ኮፒ ብዛት በአራት) ፖስታ በጠላት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸው የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎች ጥራቱን የጠበቀና ኦርጅናል መሆን ይኖርበታል፡፡
- ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ማብራሪያ ቢያስፈልግዎ በስክ ቁጥር፡- 046-220~4224/16-21234 68 ይጠቀሙ፡፡
አድራሻ፡- ወንዶ ንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ አጠገብ
በገቢዎች ሚኒስቴር የሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት