Your cart is currently empty!
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ. ሽገር ከተማ ውስጥ የታጠቅ እንዱስትሪ ዞን ጎልድ ቅርንጫፍ የውስጥ ዲዛይን ኮንስትራክሽን ሥራ ሕጋዊና በሙያው በቂ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Reporter(Oct 12, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ታጠቅ ኢንዱስትሪ ዞን ጎልድ ቅርንጫፍ የውስጥ ኮንስትራክሽን ሥራ ግዥ
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 09/2025/26
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ አ.ማ ሽገር ከተማ ውስጥ የታጠቅ እንዱስትሪ ዞን ጎልድ ቅርንጫፍ የውስጥ ዲዛይን ኮንስትራክሽን ሥራ ሕጋዊና በሙያው በቂ ልምድ ያላቸውን ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል:: በመሆኑም ከዚህ በታች የተመለከተውን የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በባንኩ ዋና መ/ቤት ናሽናል ታወር ሕንጻ 7ኛ ፎቅ (ስታዲየም ኢትዮጵያ ሆቴል ጀርባ) ግዥና ፋሲሊቲ አስተዳደር መምሪያ ቢሮ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ስታዲየም ቅርንጫፍ በመክፈል እና የገቢ ደረሰኝ ይዞ በመቅረብ ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት 2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በሚወስዱበት ወቅት የድርጅታቸውን የመስመር ወይም የሞባይል ስልክ ቁጥር በትክክል እና ግልጽ በሆነ መልኩ መጻፋቸውን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል:: በትክክልና ግልጽ ሆኖ ባልተጻፈ ኣድራሻ ምክንያት ጨረታውን በተመለከተ በስልክ ለሚተላለፍ መረጃ አለመድረስ ባንኩ ኃላፊነት አይወስድም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000.00 (ሠላሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም ቅድመ ሁኔታ በሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተራ ቁጥር 1 ላይ በተጠቀሰው አድራሻ በመገኘት ያዘጋጁትን ሰነድ ለጨረታ ሰነድ ማስገቢያ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸል።
- ጨረታው ጥቅምት 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዚያው እለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጠዋት 4፡15 ላይ ይከፈታል።
- ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 5 የተጠቀሱትን ቅድመ ሁኔታዎች ሳያሟሉ ከቀሩ ከጨረታው ይሰረዛሉ።
- ለመጫረት ፍላጎት ያላቸው ሕጋዊ ድርጅቶች ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011 558 12 04 ወይም 011 531 80 97 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
- ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊት የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።