ፀደይ ባንክ አ.ማ. ያልተከራዩትን ክፍሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 12, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የህንፃ ኪራይ የጨረታ ማስታወቂያ

ፀደይ ባንክ አማ በአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ወረዳ 07(ሰንጋተራ አካባቢ) ባስገነባው 4B+G+M+25 ህንጻ ውስጥ፡-ከምድር ወለል ጀምሮ እስከ 6ኛ ፎቅ ለንግድ ስራ ለሱቅ፣ለሬስቶራንት፣ለፋርማሲ፣ለሜዲካል ሴንተር፣ ለውበት ሳሎን፣ካፌ፣ሱፐር ማርኬት፣ ሾዉ /ዲስፕለይ ሩም ወዘተ) አገልግሎት የተዘጋጁ ክፍሎችን ቀደም ብሎ በወጣ ጨረታ ያልተከራዩትን ክፍሎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማከራየት ይፈልጋል። በመሆኑም፡-

  1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ ፀደይ ባንክ ለገሀር ቅርጫፍ ወይም በማንኛውም የፀደይ ባንክ ቅርንጫፍ በመክፈል የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ጨረታው እሰከሚዘጋበት ድርስ መ/ቤቱ በመቅረብ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2:00 እስከ 1100 ሰዓት እና ቅዳሜ እስከ 6:00 ሰንጋተራ በሚገኘው ፀደይ ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ግዠ ክፍል መውሰድ ይችላሉ። ጨረታው የሚከፈትበት ቦታና ሰዓት ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው ፀደይ ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት 16ኛ ፎቅ ሲሆን የጨረታው መዝጊያ ቀን ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ሲሆን የጨረታ መክፈቻ በተመሳሳይ ቀን ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ይሆናል።
  2. ተጫራቾች ከአንድ በላይ በሆኑ ክፍሎች መሳተፍ ይችላሉ። ሆኖም የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚወዳደሩበትን ክፍሎች ካሬ ሜትር ጠቅላላ የሶስት ወር የቅድሚያ ክፍያ የኪራይ ዋጋ መነሻ በማድረግ 2% ወይም የጠቅላላ ዋጋው 2% ከብር 500,000.00 የሚበልጥ ከሆነ ብር 500,000.00 በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በፀደይ ባንክ አ.ማ ስም ማስያዝ አለባቸው።
  3. ተጫራቾች ነጋዴዎች ከሆኑ የታደሰ እና አግባብነት ያለው የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ እንዲሁም ለትርፍ ያልተቋቋሙ ድርጅቶች ከሆኑ የታደሰ የምዝገባ ሰነድ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች ህንጻውን (ክፍሉን) ለምን ዓላማ እንደሚከራዩት መግለጽ አለባቸው።
  5. ተጫራቾች ለኪራይ የቀረቡ ክፍሎችን በተዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ሰንጠረዥ ላይ በተገለፀው ቦታ ከጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 26 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በስራ ቀን እና ሰዓት አዲስ አበባ ህንፃው ባለበት ቦታ በመገኘት ማየት ይችላሉ።
  6. የጨረታው አሸናፊ የሚሆነው ለክፍሎች በተሰጣቸው መለያ ቁጥር መሰረት በሜትር ካሬ ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ይሆናል።
  7. ተጫራቾች በፖስታቸው ላይ ስም፣ ፊርማና ስልክ ቁጥር መፃፍ አለባቸው።
  8. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0918 78 21 88 /0911383713 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
  9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-

አዲስ አበባ ከተማ ሰንጋተራ አካባቢ በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት ህንጻ

16ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር09

ፀደይ ባንክ አማ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *