Your cart is currently empty!
ሐ/ህ/ክ/መ/ት/መ/ል/ቢሮ የማሽነሪ እና ገልባጭ መኪና ኪራይ አገልግሎትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ሐትመስቢ-NCB-06-2018
ሐ/ህ/ክ/መ/ት/መ/ል/ቢሮ የማሽነሪ እና ገልባጭ መኪና ኪራይ አገልግሎትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ሕጋዊ ብቃት ያላቸውን የአገር ውስጥ ተጫራቾች ይጋብዛል። በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ፦
1. የጨረታ ሰነዱን ከዚህ በታች ከተጠቀሱት አድራሻዎች የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
2. ዋጋቸውን በመሙላትና በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ጨረታ በጋዜጣ በወጣ 16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
3. የጨረታ ሣጥኑ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ 4፡30 ከታች በተጠቀሱት አድራሻዎች ይከፈታል።
4. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የጨረታ ሰነድ ጋር አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፦
1.1. በዘርፉ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸውና ለዘመኑ ለመታደሱ ማረጋገጫ፣
1.2 ማንኛውንም የወቅቱን የመንግሥት ገቢ ግብር ለመክፈላቸው ወይም ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣታቸው ማረጋገጫ፣
1.3 በመንግሥት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያስችል ማረጋገጫ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል፣
1.4 ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል፣
1.5 የጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ የጨረታውን ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
2. ተጫራቾች የማሽነሪ እና ገልባጭ መኪና ኪራይ አቅርቦት ቦታ ሐረሪ ክልል ትራንስፖርት እና መንገድ ቢሮ ባሉት ሳይቶች መሆኑን ማወቅ አለባቸው።
3. አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% የሥራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ዋጋ በሚያቀርቡበት ጊዜ የማሽነሪ መጫኛና ማውረጃ ክፍያና ተያያዥ ወጪዎችን በማካተት ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
6. ለተጨማሪ ማብራሪያ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ መጠየቅ ይቻላል።
|
መስሪያ ቤት |
ሐ/ህ/ክ/መ/ት/መ/ል/ቢሮ |
|
ቢሮ ቁጥር |
00 |
|
ፖ.ሳ.ቁጥር |
302 |
|
አድራሻ |
ስላሴ ቤ/ክርስቲያን ፊትለፊት ነጩ ህንጻ 3ኛ ወለል |
|
ከተማ |
ሐረር |
|
ሀገር |
ኢትዮጵያ |
ሐ/ህ/ክ/መ/ት/መ/ል/ቢሮ