Your cart is currently empty!
በሲዳማ ብ/ክ/መ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን የበንሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎችን ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 13, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጽ/መሣሪያ ዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብ/ክ/መ ምስራቃዊ ሲዳማ ዞን የበንሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት 2018 በጀት ዓመት ለሴክተር መ/ቤቶች አላቂ የጽህፈት መሣሪያዎችን ባቀረቡት በግዥ ፍላጎታቸው መሠረት ሊገዛ ያቀደውን ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት
- በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ ፍቃድ ያሳደሱ
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ
- የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ባወጣው በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- በፋይናንስ ሕግ መሠረት 3 % ዊዝሆልዲንግ መክፈል የሚችሉ
- በተለያዩ ምክንያቶች በዘርፉ ሥራ ላይ ዕገዳ ያልተጣለባቸው
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 10000 (አስር ሺ) ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /cpo/ ማስያዝ የሚችሉ
- ተጫራቾች የጨረታውን ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ የሚይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ብቻ በበንሳ ወረዳ ገ/ቅ/ጽ/ቤት ከፍለው መግዛት የሚችሉ
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የዕቃ ዋጋ ላይ ቫትን ጨምሮ ያለውን ዋጋና ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች ጨረታውን ካሸነፉ በኋላ ጨረታውን ማስተካከያ መጠየቅ አይችሉም
- ተጫራቾች ጨረታ ካሸነፉ የጨረታ ማስከበሪያ ያሸነፉትን ዋጋ 10 ፐርሰንት በቼክ ወይም በሲፒኦ/ cpo/ማስያዝ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱንና የዕቃ ዋጋ መጠየቂያው ላይ ከሞሉ በኋላ ኦርጅናሉና ፎቶ ኮፒው በታሸገ ፖስታ ማስገባት አለባቸው፡፡
- መ/ቤቱ ዕቃውን የሚገዛው በአይተም ነው
- የጨረታ ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የዋጋው ማቅረቢያ ሰነዱን ኦርጅናሉና ኮፒ በሰም ታሽጎ በሁሉም ዶክሜንት ላይ ህጋዊ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ በሥራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በ16ተኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው (አስራ ስድስተኛው) ቀን በንሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት በቢሮ 9 ላይ የሚከፈት ሆኖ የተጫራቾች አለመገኘት ግን የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም
- የመ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
- የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቦታና ሰዓት ላይ ይሆናል፡፡
ለበለጠ መረጃ ፡ 0916011436/0916361005
የበንሳ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት