በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጎንደር ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ለጎ/ከ/አስ/መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 14, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

በድጋሚ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የጎንደር ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ለጎ/ከ/አስ/መንገድ ባለስልጣን አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ ተሽከርካሪዎች እና ማሽነሪዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

1. በዘመኑ የታደሰ እና ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።

3. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ ግዥ የማይመለስ ብር 300.00/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 ቀናት ጎ/ከ/አስ/ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 15 የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ለሚወዳደሩባቸው የተለያዩ ሎቶች የሚሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% ተቀባይነት ባላቸው የአፈጻጸም ዋስትናዎች ማለትም በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) በጎንደር ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ ስም የተዘጋጀ ዋስትና ማቅረብ አለባቸው::

5. ተጫራቾች ከ 1 ማሽን በላይ ዋጋ የሚሞሉ ከሆነ የሚያስይዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲደመር ከብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ ማስያዝ የሚጠበቅባቸው 500,000.00 ብር (አምስት መቶ ሺህ ብር) ብቻ ነው፡፡

6. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጎንደር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ መምሪያ ቢሮ ቁጥር 5 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ድረስ ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

7. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን 11፡30 ድረስ በአየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ክፍት ሆኖ ቆይቶ 4፡00 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 በግዥና ን/አስ/ቡ/ቢሮ ቁጥር 5 ይከፈታል፡፡ የጨረታው መክፈቻ ቀን ህዝባዊ በዓል ሳምንታዊ ዕረፍት ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተጠቀሰው ሰዓት የሚዘጋ እና የሚከፈት ይሆናል፡፡

8. ተጫራቾች የሚወዳሩበትን የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ በተለያየ ፖስታ ኮፒ እና ኦርጅናል በመለየት ወደተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

9. ተጫራቾች በዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ ውስጥ ከተዘረዘሩት 7 ማሽነሪዎች ውስጥ የሚፈልጉትን መርጠው መሙላት የሚችሉ ሲሆን አሸናፊው የሚለየው በተናጠል ዋጋ ነው፡፡

10. ማንኛውም ተጫራች የሚቀርብ ቅሬታ ካለ የጨረታው ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ማቅረብ የሚችሉ ሲሆን ከ5 የስራ ቀናት በኋላ ለሚመጣ ቅሬታ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

12. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች 058 126 0306 በመደወል ወይም ቢሮ ቁጥር 5 በአካል በመገኘት መጠየቅ ይቻላል፡፡

የጎንደር ከተማ አስ/ገንዘብ መምሪያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *