Your cart is currently empty!
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት ኤሌክትሪክ ኬብሎች እና ለመንገድ መብራት ፖል ዝርጋታ እና ጥገና ለመስራት የሚያገለግሉ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡-003/2018
አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን የግዥና ንብ/አስ/ ዳይሬክቶሬት በ2018 በጀት ዓመት ኤሌክትሪክ ኬብሎች እና ለመንገድ መብራት ፖል ዝርጋታ እና ጥገና ለመስራት የሚያገለግሉ እቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- ሎት 1 – የኤሌክትሪክ ኬብሎች፤
- ሎት 2 – ለመንገድ መብራት ፖል ዝርጋታ እና ጥገና ለመስራት የሚያገለግሉ እቃዎች፤
መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው፡–
- ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፤
- የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፤
- የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው፤
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /Tin No / ያላቸው፤
- በመንግስት ግዥና የንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ ድረ–ገጽ (WWW.PPA.gov.et)
- ተጫራቾች የሚያስዙት የጨረታ ማስከበሪያ/ CPO፡–
- ሀ. ሎት 1. የኤሌክትሪክ ኬብሎች 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ) (CPO)፤
- ለ. ሎት 2. ለመንገድ መብራት ፖል ዝርጋታ እና ጥገና ለመስራት የሚያገለግሉ እቃዎች – 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ)፤
8. ተጫራቾች በባንክ የተረጋገጠ በመ/ቤታችን ስም CPO ማስያዝ አለባች፤ሁ ነገር ግን CPO ያላስያዝ ቢኖር ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ለመወዳደር ጨረታው ከተዘጋጀ በኃላ ለሚወዳደሩበት እቃ በእስፔስፊኬሽኑ መሰረት መሆን አለበት፡፡
10. ማንኛውም ተጫራቾች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 7 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ 5ኛ ፎቅ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመቅረብና የማይመለስ 200 ብር /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
11. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን ያልጠበቀ ዕቃ ወይም አገልግሎት ካቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፡፡
12. መ/ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፡፡
13. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ፋይናንሻል ኦሪጅናል በአንድ ፖስታ እና ኮፒ አንድ ፖስታ ከዛ ደግሞ ቴክኒካል ኦሪጅናል በአንድ ፖስታ እና ኮፒ በአንድ ፖስታ ዋጋ ሞልታችሁ በተናጠል / ለየብቻው በፖስታ አድርጋችሁ የድርጅታችሁ ማህተም፣ ፊርማና የተወዳደራችሁበትን የሎት አይነት በፖስታው ላይ እየጻፋችሁ አስገቡ፤ ካልጻፋችሁበት ደግሞ ፖስታችሁ እንደማይከፈት እያወቃችሁ የተባሉተን በሙሉ በማድረግ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ወደ ህንጻው ስትገቡ በቀኝ በኩል ባለው ሊፍት 15ኛ ፎቅ ፊት ለፊት ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ፡፡
14. ጥቃቅና አነስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸው ዕቃዎች የጨረታ ሰንዱን በነፃ ለመውሰድ፡–
ሀ. ካደራጃችሁ መ/ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለባችሁ፡፡
ለ. ሰነዱን በነፃ ለመውሰድ በመመሪያው መሰረት ለምታቀርቡት ዕቃ አምራች መሆን አለባችሁ፡፡
15. ተጫራቾች መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክከል መሙላት አለባቸው፡፡
16. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ባሸነፈበት ዕቃ ወይም አገልግሎት ላይ ውል ሲገባ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት ጨረታው ተከፍቶ ውጤት ከተለጠፈ ከየሥራ ቀናት በኋላ በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መግባት አለበት፡፡
17. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት ከ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በ10ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ከ11ኛው ቀን የበዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት ውስጥ የሚከፈት ይሆናል፡፡
ማሳሰቢያ፡–
- ተጫራቾች የቀረበው ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑንና ያላካተተ መሆኑን መግለጽ አለባችሁ፤ ይህ ካለሆነ ግን መ/ቤቱ የቀረበውን ዋጋ ቫትን እንዳካተተ አድርጎ ይወስደዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት አስተዳደር ባለስልጣን ክፍለ ከተማ አራዳ ወረዳ 1 ፒያሳ/ እስታቲክስ እናት ህንጻ ፊት ለፊት ዋስትና ንግድ ማአከል 5ኛ ፎቅ ላይ ይገኛል፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-1-27-68-25 ይደውሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መብራት አገልግሎት
አስተዳደር ባለስልጣን