ኢምብሬሲንግ ሆፕ ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከጥር 01, 2025 እስከ ታህሳስ 31/2025 ያለውን የአንድ አመት የሂሳብ እንቅስቃሴ ማስመርመር ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 14, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የሂሳብ ምርመራ አገልግሎት የጨረታ
ማስታወቂያ

ኢምብሬሲንግ ሆፕ ኢትዮጵያ የተባለ ሀገር በቀል መንግስታዊ ያልሆነ የኢትዮጵያ ነዋሪዎች ማህበር በኢብሳስ የሂሳብ ስታንዳርድ /IPSAS Standard/ መሰረት የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን ህጋዊ እውቅና ባላቸው ኦዲተሮች ማስመርመር /ኦዲት ማስደረግ እንፈልጋለን፡፡

ስለሆነም እ.ኤ.አ ከጥር 01, 2025 እስከ ታህሳስ 31/2025 ያለውን የአንድ አመት የሂሳብ እንቅስቃሴ ማስመርመር እንፈልጋለን፡፡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አዲተሮች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 የስራ ቀናት ውስጥ በስራ ሰአት በድርጅቱ ቢሮ ን/ስ/ላ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 መካኒሳ ቆሬ አካባቢ በመቅረብ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን አመልካቾች ህጋዊ ፈቃድ ያላቸዉ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የፋይናንስ እና የኦዲት ሙያ ምስክር ወረቀት ያላቸው እና ተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆኑን ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

ማሳሰቢያ፦

1. ተጫራቾች የአገልግሎት ዋጋ ታክስን ጨምሮ እና የሂሳብ ምርመራውን የሚጠናቀቁበት ጊዜ በመግለፅ የጨረታ ሰነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

2. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡

3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማመልከቻ በተጠናቀቀበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት በድርጅቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ፡-
በስልክ ቁጥር ፡- 0922-5183-97 ወይም 0921-92-3476
ኢምብሬሲንግ ሆፕ ኢትዮጵያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *