Your cart is currently empty!
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ የተለያዩ የጥገና ስራዎች ሊያሰራ ላቀደው ስራዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ የተለያዩ የጥገና ስራዎች ሊያሰራ ላቀደው ስራዎች መስፈርቱን የሚያሟሉ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
- ተጫራቾች ለስራው ህጋዊ ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ፣የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ ኤጀንሲ የተመዘገቡ ምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የ2017 ዓ.ም ንግድፈቃድ ያሳደሱ ተቋራጮች መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ተጫራቾች ዋናውንና ኮፒ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ከላይ በተጠቀሰው በግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ የጥገና ስራ እና የፋይል ካቢኔት ስራ ደረጃ GC-6, BC-6 እና ከዚያ በላይ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ ህንጻ 4ኛ ፎቅ ረዳት ፋይናንስ ከፍል 51 ቁጥር ድረስ በመምጣት ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ) ብቻ በመክፈል መውሰድ ይኖርባቸዋል፤፡፡
- ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ ፣ፋይናንሽያል ሰነድ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ኮፒ በድምሩ 6 (ስድሰት) ሰነድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጨማሪም የታሸገውን 6 ፖስታ የፋይናንሽያል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግና ቴክኒካል ሰነድ ሶስቱን ፖስታ በአንድ ፖስታ በማሸግ ሁለቱን ፖስታና የCPO ፖስታውን በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ማህተብ በማድረግ ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡ ሰነዱን ከላይ በተጠቀሰው ቢሮ በለሚ ኩራ ከፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ ፋይናንስ ክፍል 55 ቁጥር በሚገኘው የጨረታ ሳጥን በ10ኛው ቀን የጨረታ ሰነዱን ቴክኒካል ሰነድ (Technical Proposal) ፋይናንሽያን ሰነድ (Financial Proposal ) ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት እስከ 7፡50 ሰዓት ድረስ ክፍት ሆኖ በዚሁ ቀን ከሰአት በኋላ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚሁ ቀን ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ላይ የቅድመ ብቃት (Technical Proposal) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ 4ኛ ፎቅ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ከዚህ ቀደም ምንም አይነት ውል ያላቋረጡ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ ውል ያቋረጡ ተወዳዳሪዎች ቢገኝ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከጨረታው ይሰረዛሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (BID BOND or BID SECURITY) ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ በባንክ የተገጋገጠ (CPO) ወይም unconditional bank guarantee በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በተጨማሪም ተጫራቾች ሞልተዉ ያስገቡት ሰነድ በሁሉም ገፆች ላይ ማህተም እና ፊርማ አለማድረግ፣ የስራ ዝርዝር እንዲሁም የስራ ዝርዝር ዋጋ (rate) ላይ የማይነበብ እና ያልተፈረመበት ስርዝ ድልዝ ካለ፤ዋጋ (rate) ያልተሞላለት የስራ ዝርዝር ዋጋ (rate) ላይ ፍሉድ መጠቀም ከተወዳዳሪነት ያሰርዛል፡፡
- ከትንሹ ግምት በታቸ እና የተጋነነ ዋጋ ያስገባ ተቋራጭ ብሬክዳውን (Break Down) ማስገባት እንደሚገደድ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡– የበለጠ ማብራሪያ ካስፈለገ ግዢ ቡድን በአካል በመቅረብ መረዳት ይቻላል፡፡
ፅ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
የለሚ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 መሪ ጤና ጣቢያ
cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx House and Building cttx, cttx Installation, cttx Machinery cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Others cttx, cttx Vehicle (garage service) cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Maintenance and Other Engineering Services cttx