Your cart is currently empty!
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግል የእስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 13, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ትራ/መን/ል/መደ001/2018
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ለ2018 በጀት አመት ለቢሮ ሥራ የሚያገለግል የእስቴሽነሪ እና የጽዳት ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
- የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
- በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡና በህግ ያልተገደቡ
- የቲን ተመዝጋቢነት ምስክር ወረቀት ያለዉ
- ለእያንዳንዱ ዕቃ ግዥ ከቢሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት የቢሮ የግዥ ንብ/ አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 6 በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- በኦንላይን የተመዘገበ
- የዕቃውን አይነት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንስ የጨረታ ሰነድን ለብቻ ለብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለተዘጋጀ የቴክኒክና የፋይናንስ ሰነድ ተጨማሪ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኤንቬሎፕ የውጭ ገጽ ዋና ኦርጂናል/ወይም⁄ ኮፒ ብሎ በመፃፍ አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- በማንኛውም ኤንቬሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት የለባቸውም፤ ስለተጫራቾች የንግድ ፈቃድ የቫት ሰነድ መልካም አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦሪጅናል እና c ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኤንቬሎፕ ሲሆን በፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ በዋናው /ኦርጅናል /ሆኖ ኮፒ ኤንቨሎፕ ውስጥ ከፋይናንሻል የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም፤
- ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በአየር የሚውል ይሆናል። ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡት በ16ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የቢሮ አድራሻ በግልጽ ፋይናንሻልና ቴክኒካል ሰነድ አንድ ላይ በተጫራች ፊት ተከፍቶ በንባብ ይሰማል ፡፡ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል፡፡ ማንኛውም የተጫራቾች ህጋዊ ወኪል በፍርድ ቤት የተረጋገጠና በኢፌድሪ/ በክልሉ መንግስት ህጐች ተቀባይነት ያለው ኦርጅናል የውክልና ሰነድ ይዞ መቅረብ አለበት ፎቶ ኮፒ ተደርጐ ብቻ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
- ማንኛዉም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት ለሚወዳደሩት ሎት ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% ከታወቀ ባንክ በሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ቼክ ወይም ከታወቀ በባንክ ዋስትና የሚቀርብ በባንክ ዋስትና ለብቻው በታሸገ ፖስታ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ/ጉ አቅራቢዎች ተጨማሪ መረጃ የሚፈልጉ ከሆነ በቢሮ ስልክ ቁጥር 011 365 9360 ዘወትር በስራ ሰዓት መጠየቅ ይችላሉ።
- ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
የቢሮ አድራሻ፡- ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጎን መሆኑን እናሳውቃለን።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ