የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላም ፀጥታ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አላቂ የቢሮ ዕቃና የፅዳት ዕቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 13, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሰላም ፀጥታ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡- አላቂ የቢሮ ዕቃና የፅዳት ዕቃዎች 
  • ሎት 2፡- ኤሌክትሮኒክስ

ስለዚህ ተጫራቾች፡-

  • የንግድ ሥራ ፈቃድ ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • የንግድ ሥራ ፈቃድ ምስክር ወረቀት ያለው/ያላት ኦርጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ግብር የገበሩበት ማረጋገጫ ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያለው እና የዘመኑን ግብር የገብሩበት ማረጋገጫ ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • በተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገበ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ አያይዞ ማቅረብ የሚችል
  • ጊዜው ያላለፈበት በአቅራቢነት በጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከመንግሥት መ/ቤት የተሰጠ ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት ኦሪጅናል ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል
  • የጨረታ ሰነዱ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ቴክኒካል ኦርጅናልና ኮፒ እና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ  በማድረግ ሁሉም ዶክሜንት ላይ የድርጅቱን ማህተም በማሳረፍና በመፈረም በሰም ለየብቻቸው አሽጎ ማቅረብ የሚችል
  • ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ 10,000 (አስር ሺህ) ብር 
  • CPO (ሲ.ፒ.ኦ) በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ስም በማሠራት ብቻውን በሰም አሽጎ ማስያዝ የሚችል
  • አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸው በተገለጸበት በ5 (አምስት) ቀን ውስጥ ውል መፈጸም እና የውል ማስከበሪያ ከሚያቀርበው ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ የተረጋገጠ CPO (ሲ.ፒ.ኦ) ማስያዝ የሚችል
  • ማንኛውንም ወጪዎች ማለትም የጉምሩክ፤ የትራንስፖርት የባንክ እና የሌሎች አገልግሎት ሰጪዎችን በራሱ ሽፍኖ ዕቃውን ማስረከብ የሚችል ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት የማይመለስ 100 (አንድ መቶ ብር ከሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊመንግሥት ሠላም ፀጥታ ቢሮ ግዥ ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ቀርበው በመክፈል ሰነዱን በመውሰድ በተዘጋጀው የጨረታ ሠነዱ ላይ የአንዱን እና ጠቅላላ ዋጋ በመሙላት ፖስታውን አሽጎ ማስታወቂያው የማይመለስ ከወጣበት ቀን አንስቶ ተከታታይ በ15 ሥራ ቀናት ውስጥ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ ግቢ ውስጥ ግዥ/ፋይ/ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 507 ባለው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን የጨረታ ሳጥን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡-

  • መ/ቤቱ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፈልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • አንድ ተጫራች ባቀረበው ዋጋ ላይ ሌላው ተጫራች ተንተርሶ መጫረት አይችልም
  • የወቅቱን የገበያ ዋጋ ያላገነዘበ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም ከቀረበም የዋጋ ትንታኔ ማያያዝ አለበት
  • ጨረታው የሚከፈተው በሥራ ቀን ቀን ካልዋለ በቀጣይ የሥራ ቀን ይሆናል።
  • ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ 0462125731 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰላም ፀጥታ ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *