የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 13, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ገንዘብ ቢሮ ለቢሮ ሥራ አስፈላጊ የሆኑ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ በግልፅ ጨረታ ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡-

  • በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው
  • የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር ያላቸው
  • የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፍኬት ያላቸው

ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ቴክኒካል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶኮፒ፣ ፋይናንሻል ኦሪጅናል 1 እና 2 ፎቶ ኮፒ፣ በA4 ወረቀት በማድረግና በማዘጋጀት እያንዳንዱን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳችሁን በተናጠል በፖስታ በማሸግ በፖስታው ውጭ የሰነዱን ዓይነት ኦሪጅናል ወይም ኮፒ መሆኑን በመፃፍ ሁለቱንም በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ብር 10,000 (አስር ሽህ ብር )ብቻ CPO ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጉዳ, የተዘጋጀ የዕቃዎቹ ዝርዝር መግለጫዎችን የያዘ ሰነድ / Specification / ሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 005 በ100 (አንድ መቶ) ብር ብቻ በመግዛት ሰነዱ ላይ በመፈረም እና የድርጅታቸውን ማህተም በማሣረፍ ለዕቃዎቹ የሚያቀርቡትን ዋጋ በድርጅቱ በዋጋ መሙያ ፎርም ላይ በመሙላት ቫትን ያካተተ ስለመሆኑ በመግለፅ ፖስታውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በ16ኛው ቀን እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 005 ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን እንዲያስገቡ እያሳሰብን ጨረታው 6፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ በ8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ቀኑ የዕረፍት ቀን ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ይከፈታል፡፡

 ማሳሰቢያ፡- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀነው ፡፡

ለበለጠ መረጃ፦ ስልክ.ቁ 046 212 1127/046 212 1126

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፋይናንስ ቢሮ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *