የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የጽሕፈት መሳሪያዎች፣ የጽዳት እቃዎች፣ ኤሌክትሮኒክስ እና የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 14, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግስት ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውል

  • ሎት 1 የጽሕፈት መሳሪያዎች
  • ሎት 2 የጽዳት እቃዎች
  • ሎት 3 ኤሌክትሮኒክስ
  • ሎት 4 የደንብ ልብስ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ሕጋዊ ተጫራቾች በጨረታ ማወዳደሪያ መመሪያ ይሆናል።

  1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ።
  2. የአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  3. የግብር መለያ ቁጥር /ቲን No/ያለው/ያላት ማቅረብ የሚችሉ ወይም የምትችል።
  4. በጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
  5. የሚገዙ ዕቃዎችን ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፌክሽን/ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች ለጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 50 /ሃምሳ ብር/ መግዛት ይቻላል
  7. የጨረታ ሰነድ የመሸጫ ጊዜ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ይሆናል።
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የሚወዳደሩበት የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% /አንድ በመቶ/ የባንክ ዋስትና ማስያዝ አለባቸው።
  9. ማንኛውም ተጫራች የዋጋ ማቅረቢያ ሀሳቡን በጥንቃቄ በመሙላት ፋይናሻል እና ቴክኒካሉን በተለያየ ፖስታ በማሽግ ኦርጅናል ዋናውን/ 1 ፖስታ ኮፒውን/ 1 ፖስታ/በማሽግ መቅረብ አለበት።
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸውን በተገኙበት ቢሮ ውስጥ በ16 ቀን ጠዋት 400 ሰዓት ታሽጐ 430 ሰዓት ይከፈታል። በዓላት ቀን ከሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
  11. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለጨረታው ዝርዝር ማስረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0577752939 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ
  12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።ማሳሰቢያ፡ናሙና የሚያስፈልጉ ዕቃዎች ናሙያ ማቅረብ ይኖርበታል።

የቤ//// ከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ እና ንግድና ገበያ ልማት ቢሮ

አሶሳ