Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በተለያዩ ፕሮጀክት ሳይቶች ላይ የሚገለገልበትን የክሬሸር ማሽን የኤሌክትሪክ ሞተር ሪዋይንዲንግ የጥገና አገልግሎት የሚሰጡ ተወዳዳሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር NCB/OCC‐108/2025
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን በተለያዩ ፕሮጀክት ሳይቶች ላይ የሚገለገልበትን
- የክሬሸር ማሽን የኤሌክትሪክ ሞተር ሪዋይንዲንግ የጥገና አገልግሎት የሚሰጡ ተወዳዳሪዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስጠገን ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት በማሟላት በጨረታው ላይ መወዳደር ትችላላችሁ።
- ተጫራቾች በጨረታው ላይ ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ሥራ ፍቃድ ያላቸው።
- ጊዜው ያላለፈበት ታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ስለመመዝገቡ እና ቲን ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሽህ) በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ጋራንቲ በኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን ስም አዘጋጅተው ከመጫረቻ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚሸጥበት የማይመለስ የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ ብር 400.00 (አራት መቶ) በመክፈል ጨረታ ሰነዱን ከኮርፖሬት ግዥ ቡደን አንደኛ ፎቅ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም. በ8፡00 ተዘግተው በዚሁ ዕለት 8፡30 ላይ ይከፈታል።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 11-439-04-22/+251 11 439-13-07
የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን (ኦ.ኮ.ኮ.)
ፊንፊኔ
cttx Construction and Water Works cttx, cttx Construction Machinery and Equipment cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Installation, cttx Machinery cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Others cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Maintenance and Other Engineering Services cttx