በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በሕጋዊ ኤጀንሲ የጥበቃ ሠራተኞችን በተለያየ የውሃ ጉድጋድ ጣቢያ በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 15, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት በሕጋዊ ኤጀንሲ የጥበቃ ሠራተኞችን በተለያየ የውሃ ጉድጋድ ጣቢያ በጨረታ አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት ድርጅታችን የሚከተሉትን መሰፈርቶች የሚያማሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

1 በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይገባቸዋል፡፡

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ተመዝጋቢ የሆኑ፣

3. ኤጀንሲው ከላይ የተጠቀሱትን የሚገልፅ ማሰረጃዎች ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒውን ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

4. ኤጀንሲው የጨረታው ዝርዝር መግለጫ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት/15/ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ ብር 500/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 9 ገቢዎች ዳይሬክቶሬት ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

5. ኤጀንሲዎች የሚያቀርቡበትን የዋጋ ማቅረቢያ ዝርዝር(ሰነድ) እና ኮፒ ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ / በፖስታ/ በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት አስራ አምስት(15) ተከታታይ የስራ ቀናት እና በስራ ሰዓት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ በአዘጋጀነው የጨረታ ሣጥን ማሰገባት ይችላሉ፡፡ 

6. ጨረታው በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በሸገር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሰበታ ከተማ ቅርንጫፍ ይከፈታል፣ ሆኖም ግን ህጋዊ ወኪሎቻቸው ያለመገኘት የጨረታውን መክፈቻ ህደት አያስተጓጉልም፣ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡

7.ኤጀንሲው ለጨረታ ማስከበሪያ 1% ብቻ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ ወይም ሲፒኦ ከጨረታው ሰነድ ጋር ማስገባት አለበት፡፡

8. የስራው አይነት ዝርዝር መግለጫ (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል፡፡

9. ዊዝ ሆልድ ታክስ ለመቁረጥ ፈቃደኛ መሆን አለባቸው፡፡

10. የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በኃላ የሚቀርብ ማንኛውም የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡

11. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡-0113-38-13-83/ 09-42-70-85-56

በሸገር ከተማ የሰበታ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *