Your cart is currently empty!
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን የመኪና መጠገኛ ጋራዥ አወዳደሮ በወርሃዊ ኪራይ ማከራየት ይፈልጋል
Reporter(Oct 15, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የመኪና መጠገኛ ጋራዥ
(Garage Shade with accessories)
ኪራይ ጨረታ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ስር የሚተዳደረው <<ዳይካክ ሁለገብ ጋራዥ ልዩ ልዩ አገልግሎቶች ከራዳ ማዕከል>> በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 07 በቤት ቁጥር 9999 (ከሸገር ዳቦ ፊት ለፊት 100ሜ ገባ ብሎ) ያለውንና አጠቃላይ ስፋቱ 885 ስኩዌር ሜትር የሆነ ሰፊና ዘመናዊ ጋራዥ ባለበት ሁኔታ በዘርፉ ከፍተኛ የጋራዥ ልምድ ላላቸው፤ የዘመኑን ግብር ለከፈሉና ማዕከሎ ያስቀመጣቸውን መስፈርቶች የሚያሟሉትን አወዳደሮ በወርሃዊ ኪራይ ማከራየት ይፈልጋል::
ጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ጋራዥ ያለበትን ሁኔታ በመጎብኘት፤ አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት በመምጣት የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመግዛት ሰነዱ ላይ ለተዘረዘሩት በቂ ምላሽ በመስጠት እንዲሁም ማስረጃዎችን በማያያዝ በአንድ ፖስታ፤ እንዲሁም በወር የሚከራይበትን ዋጋ በመሙላት በሌላ ፖስታ በተፈረመና በሰም በታሸገ ማህተም ያረፈበትን ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት ሰባት የሥራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ገቢ እንድታደርጉ የንግድ ማዕከሉ ያስታውቃል::
ማዕከሉ ሌላ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ዝርዝር የጨረታ መስፈርቶች በጨረታ ሰነዱ ላይ ተመልክቷል::
ሰነዱን አራት ኪሎ ቱሪስት ሆቴል ፊት ለፊት በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ዋናው መ/ ቤት ዘወትር ከሰኞ እስከ ዓርብ በሥራ ሰዓት ማግኘት ይቻላል::
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስ.ቁ. 0991 391 455 / 0911 866 737 ይደውሉ::