በኦሮሚያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሙያ ቢሮ የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ1ኛ ዙር ለሥልጠና የሚውል የእስቴሽነሪ፣ የኤሌክትሪክ/ ኤሌክትሮኒክስ፣ የኮንስትራክሽን፣ የጋርመንት፣ የአውቶሞቲቭ፣ ለሆቴል እና ለውበት ሳሎን ማሠልጠኛ የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 15, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

የአ/ፖ/ቴ/ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በጀት ለ1ኛ ዙር ለሥልጠና የሚውል የእስቴሽነሪ፣ የኤሌክትሪክ/ ኤሌክትሮኒክስ ፣የኮንስትራክሽን፣ የጋርመንት ፣ የአውቶሞቲቭ፣ ለሆቴል እና ለውበት ሳሎን ማሠልጠኛ የሚውሉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለዚህ

1. በሥራ መስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ወይም ለመክፈላቸው ማስረጃ የሚያቀርብ።

3. የአቅራቢነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ

5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) በባንክ በተመሰከረ ቼክ(CPO) ማስያዝ አለባቸው።

6. የአንድ ሰነድ ዋጋ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመግዛት በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ብቻ ዋጋ በመሙላት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ኮሌጁ ለዚህ ጨረታ ባዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዛው ዕለት በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል።

7. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫት ያካተተ መሆን አለበት፡፡ ይህ ካልሆነ የቀረበው ዋጋ ቫት ያካተተ እንደሆነ ተቆጥሮ ይወሰዳል።

8. የሽያጫችሁን ቫት 7.5% እና ዊዝ ሆልድ 3% የሚቆረጥ መሆኑን ልብ ይበሉ።

9. የጨረታው አሸናፊ በጨረታው ያሸነፈባቸው ዕቃዎች እሰከ በጀት አመቱ መጨረሻ ሲታዘዝ ኮሌጅ ድረስ በራሱ ወጭ ማቅረብና የዕቃው ጥራት በተጠቃሚ ባለሙያ ሲረጋገጥ ብቻ ርክክብ የሚደረግና ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል።

10. ኮሌጁ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

11. ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 022 111 5245 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ።
አድራሻ፡- አዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ አዳማ ከተማ ቀበሌ ደደቶ ኣራራ (04)

 በኦሮሚያ የሥራ ዕድል ፈጠራና ሙያ ቢሮ የአዳማ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ