Your cart is currently empty!
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን በ2018 ዓ/ም የተለያዩ መጠን ያላቸው HDPE መገጣጠሚያ፣ DC1 መገጣጠሚያ፣ C1 መገጣጠሚያ፣ ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 16, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የወላይታ ዞን የሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን በ2018 ዓ/ም
- የተለያዩ መጠን ያላቸው HDPE መገጣጠሚያ,DC1 መገጣጠሚያ C1 መገጣጠሚያ ቧንቧ እና የቧንቧ መገጣጠሚያ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለዚህ ተጫራቾች፦
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ሰርተፍኬት ማቅረብ አለባቸው::
- የዕቃ ወይም የአገልግሎት አቅራቢነት ምስክር ወረቀት በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው::
- ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200/ብር ሁለት መቶ/ እየከፈሉ ከወ/ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ቢሮ ቁጥር 13 የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሠነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ:: ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው
- ተጫራቾች አንዱን ዕቃ የሚያቀርቡበትን የመወዳደሪያ ዋጋ በታሸገ ፖስታ በማድረግ በጨረታ ሠነድ ላይ በተዘጋጀው ዋጋ መሙያ ሰንጠረዥ በመሙላት በወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ለዚህ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አስፈላጊውን ውለታ በመፈፀም ሙሉ በሙሉ ወ/ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን ድረስ በመቅረብ ገቢ ሲያደርጉ ክፍያ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
- ጨረታ ሠነድ አቀራረብን በተመለከተ 1 (አንድ) ኦርጅናል እና 1 (አንድ) ኮፒ ተዘጋጅቶ በጨረታ ሣጥን በዕለቱ በመጨመር በታሸጉ ፖስታዎች ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0465512333,0913341782, 0912138978 በሥራ ሰዓት ደውስው መጠየቅ ይችላሉ
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የወላይታ ሶዶ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ኮርፖሬሽን
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Plastic Products cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Plastic Raw Materials cttx, cttx Sanitary and Ceramics cttx, cttx Water Engineering Machinery and Equipment cttx, cttx Water Pipes and Fittings cttx