Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሰራተኞች ካፍቴሪያ ህንፃዎች ማስፋፊያ ግንባታ እና እድሳት ስራ ብቁ የሆኑ የደረጃ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን እና ህንጻ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት (Design & Construction Turn Key Basis) ለማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 16, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- SSNT-T577
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ የሰራተኞች ካፍቴሪያ ህንፃዎች ማስፋፊያ ግንባታ እና እድሳት ስራ ብቁ የሆኑ የደረጃ ሁለት እና ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ሥራ ተቋራጮችን እና ህንጻ ስራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዲዛይን እና ግንባታ የውል ዓይነት (Design & Construction Turn Key Basis) ለማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ሥራ ተቋራጮች ጨረታውን እንዲሳተፉ ይጋብዛል።
- የፕሮጀክቱ ዲዛይን እና ግንባታ ሥራው 30 ቀናት የንድፍ/Design ዝግጅት ቀናትን ጨምሮ በ270 ቀናት ውስጥ መጠናቀቅ አለበት።
- በዘርፉ ለመስራት ለ2017 ዓ.ም ከንግድ ሚኒስቴር የተሰጠ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው
- በዘርፉ ለመሰማራት የሚያስችል የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ፍቃድ ከሚሰጥ ህጋዊ አካል ለ 2017 ዓ.ም የታደሰ ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ GC/BC-2 እና ከዚያ በላይ ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ እና ከታክስ እዳ ነጻ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
- የመንግስት መስሪያ ቤቶች በሚያወጡት ጨረታ ውስጥ ለመሳተፍ የተሰጠ ጊዜው ያላለፈበት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- የሀገር ውስጥ ተጫራቾች የተሰማሩበትን የሥራ ዘርፍ የሚያሳይ ህጋዊ የሥራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉና በ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለሥልጣን የአቅራቢ እና አገልግሎት ሰጪዎች ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆን ይገባቸዋል።
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት የስራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር /አንድ መቶ ብር/ በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-T577 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዥ ከፍል በኢሜይል ማግኘት ይችላሉ። በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ስራ ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል። ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም።
ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ፎቶ ኮፒውን በተለያየ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዢ ክፍል ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ድረስ ማቅረብ አለባቸው። ጨረታው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በቦሌ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው የጨረታ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ በተመሳሳይ ቀን በ9፡00 ሰዓት ይከፈታል።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፦
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል
ስልክ ቁጥር 011-517-4552
ወ/ሮ ብርቱካን ሰሙ
ኢ-ሜይል: BirtukanS@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።