Your cart is currently empty!
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት መስኖ ውሀ አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት በኢዩ ካፌ የበጀት ለስሜን ሜጫ እና ለባንጃ ወረዳ ለቡና ልማት ማስፈጸሚያ አገልግሎት የሚውል የቨርሚ ተስቦ ትል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 02
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የግብርና ቢሮ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት መስኖ ውሀ አጠቃቀም ዳይሬክቶሬት በኢዩ ካፌ የበጀት ለስሜን ሜጫ እና ለባንጃ ወረዳ ለቡና ልማት ማስፈጸሚያ አገልግሎት የሚውል የቨርሚ ተስቦ ትል ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል። ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራች ድርጅቶች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- በዘርፉ የተሰማሩ ሆነው ማለትም የቨርሚ ተስቦ Worm /ትል/ በማቅረብ የተሰማሩ እና በዚሁ ዘርፍ ስለመሰማራታቸው ከሚመለከተው አካል የተሰጣቸው ፈቃድ እና በዘመኑ ስለመታደሱ የሚገልጽ እና ግብር የከፈሉበትን ክሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ።
- የግብረ ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- የግዥው መጠን ብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማደረግ ከኦርጅናሉ ጋር በማገናዘብ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
- የሚገዙ የቨርሜ ወርም ትል ግዥ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ እና መቅረብ ያለባቸው አስፈላጊ መረጃዎች ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00/አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ቢሮ ቁጥር 14 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት ብር ጠቅላላ የዕቃ ፣የግንባታ ወይም የአገልግሎት ዋጋ ብር በቁርጥ 50,000.00/ሀምሳ ሺብር/ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) በባንክ በተረጋገጠ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር በጥንቃቄ በታሸገ በፖስታ ማቅረብ (ጥሬ ገንዘብ) በመ/ቤቱ በህጋዊ ደረሰኝ ማስያዝ አለባቸው። ማንኛውም ተጫራች የጨረታ መወዳዳሪያ ሃሳቡን የቴክኒካል ሰነድ ዋና እና ቅጅ ለየብቻው እና የፋይናሽያል ሰነዱ እና የጨረታ ማስከበሪያውን በአንድ ዋና እና ቅጅ በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግብርና ቢሮ ግቢ ቢሮ ቁጥር 025 ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ግብርና ቢሮ የስብሰባ አዳራሽ 16ኛ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም የበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን 4፡00 ታሽጎ 4፡30 ይከፈታል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው ለመሳተፈ የሚፈለጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቤሮ ቁጥር 25 ድረስ በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582205849/0583208095/ በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ያለምንም ስርዝ ድልዝ የተሞላ ዋጋ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ይህ ካልሆነ ሰነዱ ተቀባይነት ላይኖረው ይቻላል። ባጋጣሚ የተሰረዘም ከሆነ የሞላው ድርጅት ፊርማ መኖር አለበት።
- በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ህጎችና ደንቦች በግዥ መመሪያው መሰረት ተፈጻሚ ይሆናሉ።
- ከዚህ በፊት የቨርሚ worm/ትል አምርተው ስለማቅረባቸው ከሚመለከተው አካል የጽሁፍ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ