በአቃቂ ክፍለ ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቂሊንጦ ቁ.2 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ለትምህርት ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 17, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የግዢ መለያ ቁጥር 001/2018

በአቃቂ ክ/ከተማ በወረዳ 9 ስር የሚገኘው ቀሊንጦ ቁ2 የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ለት/ቤቱ አገልግሎት የሚውሉ እቃዎችን በየሎቱ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም ለሎቱ ሲፒኦ በማስያዝ ማቅረብ የምትችሉ ተራቾች ከዚህ በታች ያሉትን አያንዳንዱ መረጃ መስፈርቶች፣ በጥንታቱ ትኩረት ሰጥታችሁ በማንበብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

  • ለሎት 1 የደንብ ልብስ 30,000.00 ብር
  • ለሎት 2. አላቂ የቢሮ ዕቃ 20,000.00 ብር
  • ለሎት 3. አላቂ የትምህርት ዕቃ 20,000.00 ብር
  • ለሎት 4. አላቂ የፅዳት እቃ 35,000.00 ብር
  • ለሎት 5. ልዩልዩ መሣሪያ 5000.00 ብር
  • ሎት 6. የሕክምና እቃዎች 5000.00 ብር
  1. በዘርፉ የተሰማሩበት የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ እና ቲን ነምበር /TIN NO/ ያላቸው።
  2. የዘመኑ ግብር የከፈሉና በአቅራቢዎች ስም ዝርዝር ላይ የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚገልጽ መረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  4. የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.አ ከላይ በተጠቀሱት የሎት አይነቶች መሠረት ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለበት።
  5. የጨረታ ሰነዱ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ የማይመለስ 400.00 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በት/ቤቱ ፋይናንስ ቢሮ ቁ.3 መግዛት ይችላሉ።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ አርጅናልና ኮፒውን በመለየት በፖስታ በማሸማ ትቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው የሚዘጋው በጋዜጣ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በሥራ ቀናት ውስጥ በ4፡00 ሰዓት ይሆናል። እንዲሁም ጨረታው የሚከፈተው በዚሁ ዕለት 4፡30 ይሆናል።
  9. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈውን ዕቃ በሚደረገው የውል ስምምነት መሠረት በራሱ ትራንሰፖርት ቂሊንጦ ቁ.2 የመጀ/ደ/ት/ቤት ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  10. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ዕቃዎች ጨረታ ከመከፈቱ በፊት የጨረታ ሰነድ ስትመልሱ ከእያንዳንዱ አላቂና ቋሚ እቃዎችን በመለየት ናሙና ሳምፕል ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪ፡- መምጣት የማይችሉ ከባድ እቃዎችን በፎቶ ከነስፔስፊኬሽኑ እንድታቀርቡልን እናሳስባለን።
  11. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሉቻቸው በተገኙበት ይሆናል።
  12. የጨረታ አሸናፊ ሆነው ከተገኙ በኋላ 10% /አስር /ፐርሰንት ባሸነፉበት ዕቃ መሠረት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል
  13. መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  14. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋጋ ዝርዝር ስትሞሉ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ እና በፍሉድ የጠፋና የተነካካ የዋጋ ዝርዝር እንዳይኖር እናሳሰባለን።
  15. ተጫራቾች በምታቀርቡት ናሙና ሳምፕል ላይ ምንም አይነት የድርጅት ማህተም ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ምልክቶች እንዳይኖር ከወዲሁ እናሳሰባለን።
  16. ለጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ ምርት ብቻ መወዳደር ይችላሉ። ነገር ግን የሀገር ውስጥ ምርት ካልሆነ እንደማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ መግዛት እና ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል። ስለሆነም የሦስትና ደብዳቤ የማንቀበል መሆኑን ከወዲሁ እንገልጻለን።
  17. ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 20198347/0913-641182 ብለው ይደውሉ።
  • አድራሻ፡- ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ፊት ለፊት ያለው ት/ቤት

በአ/ቃሊቲ ክ/ከተማ ወረዳ 09 ትምህርት ጽ/ቤት ቂሊንጦ ቁ.2 ቅድመ አንደኛና አንደኛ ደረጃ ት/ቤት