Your cart is currently empty!
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሽኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለጉራፈርዳ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት የመንገዶችን ደረጃ የማሳደግ ስራዎችን ለማከናወን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 17, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ በቤንች ሽኮ ዞን የጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለጉራፈርዳ ወረዳ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት
- ሎት 1. የገጠር ቀበሌዎችን ከወረዳው ጋር የሚያገናኙ መንገድ ከፈታ ስራ
- ሎት 2. በተለያዩ ቀበሌዎች ለሚያሰራው የመንገዶችን ደረጃ የማሳደግ ስራዎችን ለማከናወን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመስራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታ መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉት መስፈርት ማሟላት አለባቸው፡፡
1. የግንባታ ማሽነሪዎች ባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ፤ ህጋዊ ውክልና ወይም በአማራጭነት ሌሎች ባለቤትነቱን ሊገልጽ የሚችሉ ህጋዊ ሰነዶች እንዲሁም በህግ አግባብነት ካለው አካል የተሰጠ የግንባታ ማሽነሪዎችን በኪራይ ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡-
2. በግንባታ ማሽነሪዎች አቅራቢነት ብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
3. በግንባታ ማሽነሪዎች አቅራቢነት የስራ ልምድ ማቅረብ የሚችሉ
4. በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑ ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድህረ-ገፅ መመዝገብ ይኖርባቸዋል
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ certified payment(CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ የቀረበ የባንክ ዋስትና ከሆነ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና unconditional Bank Guarantee/ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ብር 100,000/አንድ መቶ ሽህ ብር/ ማቅረብ የሚችል
6. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ተከታታይ የስራ ቀናት በቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በግዥ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 500 /አምስት መቶ/ በመክፈል ሰነዱን መግዛት የሚችሉ መሆኑን፡፡
7. ተጫራቾች መ/ቤቱ በሚያቀርበው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት ተፈርሞበት ፋይናንሻል እና የቴክኒካል ሰነድ ለየብቻ በታሽገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያ ከተመለከተው የጊዜ ገደብ በፊት በጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 01 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
8. ጨረታው ማስታወቂያ በወጣ በ22ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ በተያዘው ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት የሚከፈት ሆኖ ጨረታው የሚታሸግበትም ሆኖ የሚከፈትበት ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ሆኖ ተጫራቾች በሰአቱ ባይቀርቡም የጨረታው ሂደት አያስተጓጉልም፡፡
9. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 19 33 15 42 እና 09 10 15 11 28 መጠየቅ ይቻላል።
የጉራፈርዳ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት /ቢፍቱ/