የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል የFire Extinguisher weight 5Kg Co2, External Fire hydrant Compression and Fire hydrant hoe Reel ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 17, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/SM/135/2025

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ፕሮጀክት ግንባታ አገልግሎት የሚውል የFire Extinguisher her weight 5Kg Co2, External Fire hydrant Compression and Fire hydrant hoe Reel ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የዕቃው አይነት

 

የፕሮጀክት ስም

 

የጨረታ ቁጥር

 

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ  መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

Fire Extinguisher her weight 5Kg Co2, External Fire hydrant Compression and fire hydrant hoe Reel

ለሐረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ፕሮጀክት

DCE/ SM/153/2025

 

ጥቅምት 26/2018 . 400 ሰዓት

 

ጥቅምት 26/2018 . 415 ሰዓት

 

100,000.00

 

ስለሆነም፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው እንደተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠና የተረጋገጠ (C.P.O) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይቻላል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታዲየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011440-3434 ማዞሪያ 0114-42-22-70/71/72 E-mail አድራሻ info@dce-et.com የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com  ፖ.ሳ.ቁ 3414
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *