Your cart is currently empty!
የማ/ኢ/ከ/መንግሥት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በጥቅል ግዥ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 17, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም
የማ/ኢ/ከ/መንግሥት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በጥቅል ግዥ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች ሕጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።
በመሆኑም፡-
- ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕድሳት የፈፀሙ፣ እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- ከፋይነት /ቲን እና የተጨማሪ እሴት ታከስ ከፋይነት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ ከግዥው ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ፣
- ከሚመለከተው የመንግሥት ተቋም ኦንላይን (Online) ሲስተም የምዝገባ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የሚሞሉት የአንዱ ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይንም ያላካተተ መሆን ይኖርበታል።
- ከ50,000 (ሃምሳ ሺ ብር) በላይ የሚጫረቱ ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ ማያያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሠረት የሚወዳደሩበትን ዋጋ በመሙላትና በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማድረግ ዋናውንና አንድ አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾቾ ቴክኒካል ፋይናንሻል 1 ኦርጂናል እና 1 ኮፒ በማዘጋጀትና ስፔስፍኬሽን ለሚያስፈልጋቸው በተቀመጠው ስፔስፍኬሽን መሰረት በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው።
- ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ለተወደደሩባቸው ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ለያንዳዳቸው ናሙና ማቅረብ አለባቸው።ናሙና ያልቀረበባቸው የዕቃ ዓይነቶች ከውድድር ውጪ ይሆናሉ።
- ተጨረቾች የጨረታውን ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ብር 5000.00 /አምስት ሺ ብር / ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታውን ዝርዝር የያዘ ሰነድ ከመስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ይዘው በመቅረብ የማይመለስ 150 (አንድ መቶ ሀምሳ ብር) ብቻ በመክፈል 9 ቁጥር ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የዚህን የጨረታ ሰነድ መመሪያ በሚገባ በመረዳት የጨረታ ሰነዳቸውን ሞልተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ የመስኖ ተቋማት ልማት አስተዳደር ኤጀንሲ ግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት 9 ቁጥር ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ይከፈታል። በ15ኛው ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን ይከፈታል።
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ እንደሚሆኑ እና ለወደፊትም በመንግስት ዕቃ አገልግሎት ግዥ እንዳይሳተፉ እንደሚደረግ እና ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና እንደሚወረስ ማወቅ አለባቸው።
- ተጫራቾች ይፋ በሚደረገው ውጤት መሰረት ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች አሸናፊነታቸው ተገልፆ ውል በተፈራረሙ በ15 ቀናት ውስጥ ወልቂጤ በሚገኘው የመስኖ ተቋማት ልማትና ስተዳደር ኤጀንሲ መጋዘን ማስረከብ አለባቸው።
- ኤጄንሲው በግዥው ዝርዝር ፍላጎት ላይ 20% የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
- ኤጀንሲው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ 251 11 365 8470
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት መስኖ ተቋማት ልማትና አስተዳደር ኤጀንሲ ወልቂጤ