ገነት ሆቴል በግቢው ውስጥ ያሉትን ነባር የሬስቶራንት ክፍል፣ የመጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች፣ ባርና በረንዳ፣ የአዳራሽ መግቢያ አካባቢ ቦታዎችን የግንባታ እድሳት ስራን ለማሰራት ብቁ የሆኑ የሃገር በቀል የህንጻ ወይም የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5 (አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 17, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የግንባታ ጥገና ስራ የጨረታ ማስታወቂያ

ገነት ሆቴል በግቢው ውስጥ ያሉትን ነባር የሬስቶራንት ክፍል፣ የመጸዳጃ እና መታጠቢያ ክፍሎች፣ ባርና በረንዳ፣ የአዳራሽ መግቢያ አካባቢ ቦታዎችን የግንባታ እድሳት ስራን ለማሰራት ብቁ የሆኑ የሃገር በቀል የህንጻ ወይም የጠቅላላ ስራ ተቋራጭ ደረጃ 5 (አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑትን ድርጅቶችን በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እንዲሁም የሰው ኃይል፣ ማሽን እና የግንባታ ግብዓቶችን ማሟላት የሚችሉ ስራ ተቋራጮች ስራውን ለማከናወን በግልፅ ጨረታ ውድድር መሳተፍ ይችላሉ፡፡

  1. በህንጻ ወይም በጠቅላላ ስራ ተቋራጭነት ደረጃ -5 (አምስት) እና ከዚያ በላይ የሆኑ፤
  2. የ2017/18 ዓ.ም ዘመን የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፊኬት (VAT) ያላቸው፤
  4. የግብር ከፋይ ምዝገባና ሰርተፊኬትና መለያ ቁጥር (TIN) ሰነድ ያላቸው፤
  5. የአቅራቢዎች ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፤
  6. ተጫራቾች ስለጨረታው ሙሉ ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ታሳቢ የሚደርግ 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ጊዜ ውስጥ ከድርጅታችን የፋይናንስ ቢሮ ክፍል የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 500.00 (አምስት መቶ ብር) ከፍለው መውሰድ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ “ለገነት ሆቴል” በሚል በማሰራት ከቴክኒካል ሰነድ ጋር ለብቻው በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች የቴክኒካል ሰነድ እና ስራውን የመስሪያ ፋይናንሻል ሰነድ ለእያንዳቸው አንድ ኮፒ በማዘጋጀት በተናጠል ለየብቻ በማሸግ በጥቅል በአንድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማደረግ እስከ አስራ አምስተኛው (15) ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የፍይናንስ ክፍል ቢሮ ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡ አስራ አምስተኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ የጨረታው መክፈቻ በቀጣይ ባለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል፡፡
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ተወካዮች ባሉበት በአስራ አምስተኛው (15) በ8፡30 ሰዓት ድርጅቱ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
  10. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- አ.አ ከሜክሲኮ ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- 011-550-4701/ 09-11 25 06-41/ 09-39-50-00 00

ገነት ሆቴል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *