በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የማስታወቂያ ቁጥር /ዕዝ ሜንቴናንስ

መምሪያ ግዥ B‐1/2018 /

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

  1. የተለያየ ሞዴል ያላቸው ቶዮታ ተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ ዕቃ
  2. የተለያየ ሞዴል ያላቸው ኮሜርሻል ከባድ ተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ ዕቃ
  3. የተለያየ ሞዴል ያላቸው የመኪና ጎማዎች
  4. ለጦር መሣሪያና የጦር መሣሪያ ለጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች የሚውል አላቂ የጋራዥ መሥሪያ ዕቃዎች

ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ሕጋዊ ተጫራች በጨረታው ሊወዳደር ይችላል፡፡

  1. ተጫራቾች ለሚረቱባቸውየጨረታ ዓይነቶች ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው በአቅራቢነት ስለመመዝገባቸው የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ከፋይነት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
  4. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ማቅረብ አለባቸው፡፡
  5. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ለእያንዳንዱ ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ በጨረታ ሰነዱ ላይ በተገለፀው መመሪያ መሠረት በባንክ የተረጋገጠ CPO ማቅረብ ይኖርባቸዋል..
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ የዕቃውን ዓይነት ኤንቨሎፑ ላይ በግልፅ መፃፍ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ ብር 400.00 በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ግዥ ቢሮ መግዛት ይቻላል፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው /ዕዝ /መምሪያ 1 ፎቅ ላይ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጨረታው ኅዳር 2 ቀን 2018 . ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዕለቱ 430 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ዕዝ /መምሪያ ı ፎቅ ላይ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡
  10. አሸናፊ ተጫራቾች ውል ሲፈፅሙ የመልካም ሥራ አፈፃፀም ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ወጭ በማጓጓዝ እና በማራገፍ ቶጋ መከላከያ ሠራዊት ካምፕ በሚገኘው የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ ግምጃ ቤት ማስረከብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  11. ከመሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ እንዲሁም 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ የመግዛት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁፕር 046 328 0019 ይደውሉ

የደቡብ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሜንቴናንስ //


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *