Your cart is currently empty!
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት የቢሮ አላቂ ዕቃ የፅህፈት መሳሪያ ግዥ፣ የቢሮ ኤሌክትሮኒክስ ግዥ፣ ጀነሬተር ግዥ እና 100 ሲሲ ሞተር ሳይክል ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎት የሚሆኑ የተለያዩ ዕቃዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
ማለትም፡–
- ሎት 1 የቢሮ አላቂ ዕቃ የፅህፈት መሳሪያ ግዥ
- ሎት 2 የቢሮ ኤሌከትሮኒክስ ግዥ
- ሎት 3 ጀነሬተር ግዥ
- ሎት 4 100 ሲሲ ሞተር ሳይክል ግዥ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት
- የዘመኑ ግብር አጠናቆ የከፈሉ ስለመሆኑ ማስረጃ የሚያቀርብ የምታቀርብ
- በመስኩ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ ያላት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት (ቲን ነምበር የለው)
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 1ኛ ሎት1 ለተመደበው ለፅህፈት መሳሪያ ብር 20,000፣ 2ኛ. ሎት 2 ለተመደበው ለኤሌከትሮኒክስ ብር 20,000፣ 3ኛ ሎት 3 ለተመደበው ለጀነሬተር ብር 20,000፣ 4ኛ. ሎት 4 ለተመደበው 100 ሲሲ ሞተር ብር 50,000 ህጋዊ ዕውቅና ካለው የፋይናንስ ተቋም የጨረታ ማስከበሪያ አያይዞ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ 300/ ሶስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እየሳወቅን ሰነዱን አንድ ኦርጂናልና አንድ ኮፒ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ ቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ በስልጤ ዞን ላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ቢሮ ቁጥር 9 ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላል፤
- የጨረታ ሳጥኑ ሰነድ ማስገቢያ የጊዜ ሰሌዳ በተጠናቀቀበት እለት ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቀኑ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል።
- አሸናፊው ድርጅት ማሸነፉን በደብዳቤ ካሳወቅንበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 03 የስራ ቀናት ውስጥ ለፅ/ቤታችን ድረስ በመምጣት ውል መግባት ይኖርባችኋል።
- አሸናፊው ድርጅት ውል የገባበትን ዕቃ ውል በገባበት ጊዜ ውስጥ እስከ ላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ፅ/ቤት ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይኖርበታል።
- በጨረታው ዕቃዎችን ለማቅረብ የምትወዳደሩ ተጫራቾች ያሸነፋችሁትን ዕቃ በጨረታ ስፔፍኬሽን መሠረት 1ኛ ደረጃ ጥራት ያላቸው፣ አስፈለጊውን ማቴሪያሎች እና መረጃ፤ ዶክመንቶች የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- ማንኛውም አሸናፊ ድርጅት የጥራት ችግር ያለበት እና ያልተሟላ መረጃ የቀረቡበት ዕቃዎች በሙሉ መልሰው ጥራት ያለውን እና መረጃ የተሟላ ዕቃ ማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስ.ቁጥር 09 13 17 02 12/09 33 43 49 98/0926 9449 00 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በስልጤ ዞን የላንፉሮ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Energy, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Generators cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Stationery cttx, cttx Tri Wheeler, Electromechanical and Electronics cttx, Motorcycles and Bicycles Purchase cttx, Power and Electricity cttx