በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ለ2018 ለሥራ የሚገለገልበትን Gs Fitting በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

ጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መስተዳድር የቢሾፍቱ ከተማ የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅት 2018 ለሥራ የሚገለገልበትን

  • Lot:- 1 Gs Fitting በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትይፈልጋል፡፡

የሚከተለውን የጨረታ መስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡

  1. ህጋዊ እና የታደሰ የ2018 ንግድ ፍቃድ ያላቸው፡፡
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚልማት ሚንስቴር ወይም በሌላም በሚመለከታቸው ፍቃድ ሰጪ አከላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው ተጫራቾች ብቻ መካፈል ይችላሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀን ድረስ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል በመቤቱ ቀርቦ መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ለጨረታው ማስከበሪያ ጠቅላላ ካቀረቡት የዕቃ ዋጋ ብር 2% በተረጋገጠ ባንክ (CPO) በድርጅቱ ስም አሰርቶ ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችል፡፡
  6. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የእቃውን ስፔሲፊኬሽን ከድርጅቱ በቀረበው መሠረት በግልፅ በመፀፍና ዕቃው ላይም በግልፅ መታየት ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ሲያቀርቡ ቫት ያጠቃለለና ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችን አሟልተው በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ የቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት ቀርቦ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ 15ተኛ ቀን አስከ ቀኑ 800 ሰዓት ማስገባት እና ተዘግቶ በዛው ቀን 830 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ በእለቱ በአል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውንና ሙሉ አድራሻቸውን በትክክል ጽፈው መፈረም አለባቸው፡፡
  9. ድርጅቱ ከሰጠው ስፔስፊኬሽን ውጪ ማስተካከያ ማድረግ እና መሰረዝ (Material Devation) አይቻልም፡፡
  10. ተጫራቾች በድሮጅቱ በዋጋ ማቅረቢያ የድርጅቱ ኦርጅናል ማህተም ቢሾፍቱ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅት የሚል ማህተም ባረፈበተ ላይ ብቻ የዕቃ ዋጋዎችን ሞልቶ ማቅረብ አለበት፡፡ ከድርጅቱ ዋጋ ማቅረቢያ ውጪ የሚመጡ ሰነዶች ዋጋ የላቸውም፡፡
  11.  ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  12. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ድርጅታችን ግዥ እና ፋይናንስ ዳይሬክተር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-437-16 83 ደውለው ማረጋገጥ ይችላሉ፡፡

ቢሾፍቱ ከተማ ልዩ 1 ደረጃ የመጠጥ ውሃ

እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *