በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል 2018 በጀት ዓመት ለተኝቶ ታካሚ ህሙማንና ለሆስፒታሉ ሠራተኞች አገልግሎት የሚውል እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 18, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል 2018 በጀት ዓመት ለተኝቶ ታካሚ ህሙማንና ለሆስፒታሉ ሠራተኞች አገልግሎት የሚውል

1. የበሰለ ምግብ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በየስድስት ወሩ የጥራት ሁኔታው ተረጋግጦ ውል እየታደሰ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ የፌዴራል ጤና ሚኒስቴር ባወጣው የሆስፒታሎች ሪፎርም መሠረት ህክምና-ነክ ያልሆኑ አገልግሎቶች በኮንትራት/በውል ለሶስተኛ ወገን የተላለፈ ህክምና ነክ ያልሆነ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራትና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

2. የተለያዩ የፅህፈት መሳሪያዎች

3. የተለያዩ የንፅህና መገልገያ ዕቃዎች

4, የተለያዩ የዉሃ የቧንቧ ዕቃዎች

5. የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት እና ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

6. ስለዚህ በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፁው መስፈርት መሠረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ

7. ተጫራቾች በዘርፉ አግባብና ህጋዊ የሆነ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ኦሪጅናል እና ኮፒ፤ የመንግስት አገልግሎት ግዥ በአቅራቢነት ለመሳተፍ የሚያስችል የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ኦሪጅናልና ኮፒ እና የዘመኑን ግብር የከፈሉና የግብር ክፍያ የምስክር ወረቀት/Tin Number/ኦሪጅናል እና ኮፒ በተለያየ ፖስታ ካሽጉ በኋላ በአንድ እናት ፖስታ በማሸግ ከመጫረቻ ስነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8. እያንዳንዳቸው ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000.00/ሰላሳ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተረጋገጠ /CPO/ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ደረሰኝ/RV/ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡

9. የተጫራቾች የካፒታል መጠን ቢያንስ 500,000.00/ አምስት መቶ ሺህ ብር ብቻ በባንክ ስለመኖሩ የባንክ ስቴትመንት መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡

10. ተጫራቾች የሚወዳድሩበት ዋጋ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገፅ ፊርማና የድርጅቱን ማህተም በማኖር ዋናውን ሰነድ በአግባቡ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ውስጥ በማድረግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በግልጽ ኤንቨሎፑ ላይ በመፃፍ ለዚሁ በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ታክስን/VAT/ የሚያካትት መሆን አለበት፡፡

11. የጨረታው ዶከመንት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በመደበኛ የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 300/ሦስት መቶ ብር/ ከሆስፒታላችን ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብና በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መውሰድ ይቻላል፡፡

12. የምግብ አቅራቢ ተጫራቾች ለሥራው የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን በግላቸው ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

13. የጨረታው ዶክመንት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድራሻ በመፃፍ ሕጋዊ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ በአየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ተጫራቾች –

ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 1. በ16ኛው የሥራ ቀን

ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 2. በ17ኛው የሥራ ቀን

ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 3. በ18ኛው የሥራ ቀን

ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 4. በ19ኛው የሥራ ቀን

ከላይ ለተዘረዘሩት ለተራ ቁጥር 5. በ20ኛው የሥራ ቀን፡ከጠዋት 3፡00-4፡00ሰዓት ባለው በሆስፒታላችን ግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ክፍል ለዚህ አገልግሎት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የመጫረቻ ፖስታ ማስገባት ይችላሉ፡፡

14.ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ቦታ ማለትም ከላይ ለተዘረዘሩት –

ለተራ ቁጥር 1. በ16ኛው የሥራ ቀን

ለተራ ቁጥር 2. በ17ኛው የሥራ ቀን

ለተራ ቁጥር 3. በ18ኛው የሥራ ቀን

ለተራ ቁጥር 4. በ19ኛው የሥራ ቀን

 ለተራ ቁጥር 5. በ20ኛው የሥራ ቀን፡ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ላይ የታሸገው የጨረታ ሳጥን ይከፈታል፡፡

15. ተጫራቾች በጨረታ መከፈቻ ሰዓት ያለመገኘት የጨረታውን ሂደት አያስተጓጉልም፡፡

16. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለተጨማሪ ማብራራያ በስልክ ቁጥር፡- 09-11-58-92-26/09-10-03-51-29 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

በጋሞ ዞን ጤና መምሪያ የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል