Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ያላቸውን የሒሣብ መርማሪ ድርጅቶችን (የኦዲት ድርጅቶችን) አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የሒሣብ ምርመራ ጨረታ
ማስታወቂያ
የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ማስፋፊያ ኤጀንሲ ህጋዊ የሙያ ፈቃድ ያላቸውን የሒሣብ መርማሪ ድርጅቶችን (የኦዲት ድርጅቶችን) አወዳድሮ ኦዲት ማስደረግ ስለሚፈልግ፤ በአዲስ አበባ፣ በገላን፣ በአሰላ ከተማ የሚገኘውን የኦሮሚያ የግብርና ሕብረት ሥራ ማህበራት ፌዴሬሽን ኃ/የተ የህ/ሥራ ማህበር የ2017/2018 ዓ.ም ሒሳብ በጨረታ አወዳድሮ ማስመርመር (ኦዲት) ማስደረግ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በዚህ የሥራ መስክ ፈቃድ ያላቸውንና በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ሁሉ መሳተፍ የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ከዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው፡፡
1. ስለ ጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ በአዲስ አበባ ከተማ ሣር ቤት በሚገኘው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ቢሮዎች ግቢ ውስጥ የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ የግዢ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር አጋዥ የሥራ ሂደት ቀርበው የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች ሒሣቡን ለመመርመር የሚያስከፍሉትን ዋጋ መጠንና ሥራውን ጀምረው የሚያጠናቅቁበትን ጊዜ ሠሌዳ ከጨረታው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች ከሚመለከተው መ/ቤት የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ያላቸው፣ የዘመኑን የሥራ ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማረጋገጫ እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
4. የሒሳብ ምርመራውን ሪፖርት በአፋን ኦሮሞ እና በእንግሊዘኛ ቋንቋ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5 ተጫራቾች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የጨረታ ሠነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በሚቀጥለው ቀን ማለትም አስራ አንደኛው የሥራ ቀን ላይ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች በሕብረት ሥራ ማሕበራት የሂሳብ ምርመራ ልምድ ያላቸውና በክልሉ የሥራ ቋንቋ በአፋን ኦሮሞ የተዘጋጀውን የመተዳደሪያ ደንብ፤ ቃለ ጉባኤዎች፤ የሂሳብ መዛግብቶችንና ሰነዶችን ማንበብና መረዳት የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
7. ኤጀንሲው ለሥራው የተሻለ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር 09 11 97 05 94/ 09 34 04 06 05
የኦሮሚያ ሕብረት ሥራ ማህበራት ማስፋፊያ ኤጀንሲ