Your cart is currently empty!
የደቡብ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፌዴሬሽን ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጓሮ አትክልት ዘር ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 001/2018
የደቡብ ገበሬዎች ኅብረት ሥራ ፌዴሬሽን ለአርሶ አደሮች ለማቅረብ የተለያዩ የጓሮ አትክልት ዘሮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች እያንዳንዱን የጓሮ አትክልት ዘር አንዱን ኪሎ ግራም በስንት ብር ሊሸጡ እንደሚችሉ የመወዳደሪያ ዋጋ በመሙላት እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
በዚሁ መሠረት:-
- በዘርፉ ሕጋዊ አስመጪነት የንግድ ፈቃድ ያለው፣የዘመኑን ግብር ከፍሎ የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው፣
- ከሚመለከተው ክፍል የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣
- ተጫራቾች ዘሩን ወደ አገር ውስጥ ሲያስገቡ ከኢፌዲሪ ግብርና ሚኒስቴር የተሰጣቸውን የብቅለት እንዲሁም የጥራት ማረጋገጫ ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ /CPO/ ብር 50,000 (ሀምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፣
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የጓሮ አትክልት ዘር የዝርያውን ዓይነት በተመለከተ፡–
- የቀይ ሽንኩርት ዝርያ ሬድ ቦምቤ፣ ሬድ ክሮይል፣ ሬድ ኪንግ፣ ኒፍቶን፣ሩሴት፣ሆላንድ፣ሲሪያል
- የቲማቲም ዝርያ ሮማ ቪኤፍ፣ ገሊሊያ፣ ቬነስ፣ ቫርነም፣ኮምቶ፣ምንካ፣ሻንቲ፣ማርግሎቭ
- የጥቅል ጎመን ዝርያ ኮፐንሀገን፣ቫንደግ፣ዩሮ፣ቪክቶሪያ፣ላንዳኒ
- የተዳቀሉ የቃሪያ ዝርያዎች፣
- የካሮት ዝርያ ናንተስ፣
- የቆስጣ ዝርያ ፎርድሁክ ጂያንት፣
- ቀይ ስር ዲትሮይድ ዳርክ ሬድ፣
- የሰላጣ ዝርያ ግሬትሌክስ ወይም ፓሪስ አይስላንድ በሚል ስሙን በመጥቀስ የተመረተበትንም አገር በግልጽ ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
 
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን የጓሮ አትክልት ዘር ዓይነት እና የዝርያ ሁኔታ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ናሙና ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚቀርበው ዋጋ በየዝርያው ተለይቶ የአንድ ኪሎ ግራም መሸጫ ዋጋ ሊሆን ይገባል፡፡
-  የሚቀርበው የጓሮ አትክልት ዘር ዝቅተኛ የብቅለት መጠኑ (Germination) እና ዝቅተኛ የጥራት መጠኑ (Purity) ሁኔታ፦
- ለቀይ ሽንከርት Germination 80% እና Purity 97%
- ለቲማቲም Germination 85% እና Purity 98%
- ለጥቅል ጎመን Germination 85% እና Purity 98%
- ስካሮት Germination 80% እና Purity 97%
- ለቆስጣ Germination 80% እና Purity 97%
- ለሰላጣ Germination 80% እና Purity 98%
- ለቀይ ስር Germination 85% እና Purity 98%
 
- የጓሮ አትክልቱ ዘር እንደአውሮፓ አቆጣጠር በ2025 የተመረተና የአገልግሎት ማብቂያ ጊዜውም (Expired date) ከ2028 ያላነሰ ቢሆን ይመረጣል፡፡
- ተጫራቾች የጓሮ አትክልቱን ዘር የሚያቀርቡበትን የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ በስንት ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ እንደሚያስረክቡ በዋጋ ማቅረቢያው ላይ ግልፅ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚሸጡበትን ዋጋ በማወዳደሪያ ቅፅ |ፕሮፎርማ/ ላይ በመሙላት በኤንቨሎፕ አሽገው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ11ኛው ቀን በሀዋሳ ከተማ በፌዴሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት ከጠዋቱ 3፡30 እስከ 6፡30 ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በ11ኛው ቀን በሀዋሳ ከተማ በፌዴሬሽኑ ዋና ጽ/ቤት ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፡፡ ከ11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ይፈፀማል፡፡
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ሀዋሳ ከተማ ሞሀ የስስላሳ መጤቶች ፋብሪካ አጠገብ
ስልክ ቁጥር 0462209894/8210/0935979146/0940289586
ፋክስ 0462214837
የደቡብ ገበሬዎች ኅብረት ስራ ፌዴሬሽን