Your cart is currently empty!
መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት ጠቅላላ ከሚጠቀምበት 126,517 ሜትሪክ ቶን የታጠበ 150,239 ሜትሪክ ቶን ያልታጠበ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለምርት አገልግሎት የሚውል የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል
አወዳድሮ ለመግዛት የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
ክፍል አንድ
መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ለምርት አገልግሎት ጠቅላላ ከምንጠቀምበት 126,517 ሜትሪክ ቶን የታጠበ 150,239 ሜትሪክ ቶን ያልታጠበ የሀገር ውስጥ የድንጋይ ከሰል አቅራቢዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሰረት የጨረታ ሰነዱን መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ አዲስ አበባ ስታድየም ወጋገን ህንፃ 3ኛ ፎቅ በሚገኘው ቢሮአችን ወይም መቐለ ዋና መስሪያቤት በአካል በመገኘት መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
በዚህ መሰረት ተጫራቾች
1. በጨረታው የሚሳተፉ ድርጅቶች የከሰል ድንጋይ በማምረት በዘርፉ የተሰማሩ መሆናቸው የሚገልፅ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆናቸው፣ የመዐድን ፈቃድና የመሬት ይዞታ ሰርተፊኬት የሚገልፅ ማስረጃ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የታጠበ የድንጋይ ከሰል ለሚያቀርቡ ደግሞ የድንጋይ ከሰል ማጠቢያ ፋብሪካ ባለቤት መሆናቸውና የስራ ፈቃድ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
2. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ ዋስትና ብር 1,000,000 (አንድ ሚልዮን ብር) በመሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ(CPO) ወይም ባንክ ጋራንቲ ለብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ከላይ በተራ ቁጥር 2 ከተጠቀሱት ማስረጃዎች ጋር በማያያዝ የድርጅታቸውን አርማና ማህተም ያለው ደብዳቤ በመፃፍ ለጨረታ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች ከዚህ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ ጋር አብሮ ከተገለፀው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ያቀርቡትን የሀገር ውስጥ ድንጋይ ከሰል (የታጠበ /ያልታጠበ) በጨረታው ቀን ወይም ከዚያ በፊት በራሳቸው ወጪ ለምርመራ ናሙና (ሳምፕል) ቢያንስ 5 ኪ.ግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ (ናሙናው የሚቀርበው መቀሌ በሚገኘው ዋና ፋብሪካ ይሆናል)፡፡
5. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያቸውና በተራ ቁጥር 2 እና 3 ላይ የተጠቀሱት ሰነዶችና በተራ ቁጥር 4 የተጠቀሰውን ናሙና (ሳምፕል) እስከ ህዳር 02/ 2018 ከሰዓት በኋላ 8፡00 ሰዓት ድረስ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ሰነዳቸው መቀሌ በሚገኘው የፋብሪካው ዋና መስሪቤት 3ኛ ፎቅ ቁጥር 15 ስለሚገኝ የግዥና አቅርቦት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
6. ጨረታው በእለቱ ህዳር 02/ 2018 ከሰዓት በኋላ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 2000 (ሁለት ሺህ ብር) በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
8. ፋብሪካው ጨረታው በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር +251344405806/+251912502596/ +251914729516 ወይም procurementmessebocement2026@gmail.com መጠቀም ይቻላል፡፡
መሰቦ ሲሚንቶ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማ