Your cart is currently empty!
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሊሰራ ላቀደው የ01 ቀበሌ ከተማ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ኮብልስቶንና ድች /Cobblestone and Ditch Work/ ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መንገዱን ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በ2018 በጀት ዓመት ሊሰራ ላቀደው የ01 ቀበሌ ከተማ ውስጥ ለውስጥ መንገድ ኮብልስቶንና ድች/ Cobblestone and Ditch Work ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መንገዱን ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች በሙሉ እንድሳተፉ እንጋብዛለን።
- የኮንስትራክሽን መሣሪያዎችን የማከራየት ፍቃድ ያላቸው ወይም በጠቅላላ ሥራ ተቋራጭነት ከደረጃ 5 እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው ሆነው ኮቢሊስቶንና ድች ሥራ ላይ ከዚህ በፊት የሠሩበት የስራ ልምድ ያላቸው፣
- ተጫራቾች አግባብነት ያለው ለዘመኑ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሠርተፍኬት፣ የግብር ከፋይ ሠርተፍኬት እና በጨረታ መወዳደር የሚያስችል የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ እንዲሁም ከመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያሳይ ሠርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ገልባጭ መኪናዎች የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ኤጀንሲ የውል ማስረጃ የተረጋገጠ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሊብሬ ውክልና ማቅረብ ይኖርበታል።
- ተጫራቹ ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት ቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና/ኦርጅናል ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው። ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- የጨረታ ማስከበሪያ/bid security/ 1% በተጫራቹ የተሞላ የፕሮጀከቱ ጠቅላላ ዋጋ /በባንክ የተረጋገጠ ዋስትና /bank guarantee/ወይም የክፍያ ማዘዣ/cpo/ በጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከመጫረቻ ሰነድ ወይም የቴክኒካል ዶክመንት ጋር ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የሥራ ቦታ/site/ በራሳቸው ወጭ አይተው /Vist/ ማረጋገጥ አለባቸው።
- ተጫራቾች በተቀመጠው መመሪያ መሠረት ህጋዊ ፍቃዳቸውና ተ.ዕ.ታ /VAT/ የተመዘገቡበትን ሰርተፍኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ20) ሃያ/ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 1000 /አንድ ሺህ ብር/ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጭሬ ወረዳ ገቢዎች ባ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሰረት ተሞልተው ጨረታ ማስከበሪያ /bid bond security/ ፋይናንሻል አንድ ዋና ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴክኒካል ሰነድ በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በትልቁ ፖስታ ውስጥ ተካተውና በሁለቱም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ21ኛው ቀን ከጧቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጭሬ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። የጨረታ ማስከበሪያው የቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 የሚከፈት ይሆናል።
ማሳሰቢያ፦
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ጨረታው የሚከፈትበት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ 0910740670/0916651155/0989925580
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጭሬ ወረዳ ከተማ ማዘጋጃ ቤት