አቢሲንያ ባንክ አ.ማ መኖሪያ ቦታ ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Oct 19, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ

አቢሲንያ ባንክ አ. ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘውንና ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ የተመላክተውን የማይንቀሳቀስ የመያዣ ንብረት በአዋጅ ቁጥር 97/1900 እንደተሻሻለው ለባንኮች በተሰጠው ስልጣን መሠረት ንብረቱ በሚገኙበት ቦታና ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። 

ተጫራቾች ለጨረታው ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደንቦች መገንዘብ ይኖርባቸዋል።

  • ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም ሲፒኦ በአቢሲንያ ባንክ አማ ስም ለጨረታ ማስከበሪያ በማስያዝ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
  • የጨረታው አሸናፊ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 15 (አስራ አምስት) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ከፍሎ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
  • በእነዚህ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል። በጨረታው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲ... ይመለስላቸዋል።
  • ተበዳሪው የንብረት ዋስትና ሰጭው በሐራጁ ቀንና ሰዓት ጨረታ በሚካሄድበት ቦታ መገኘት የሚችሉ ሲሆን በጨረታው ባይገኙም ግን ሐራጁ በሌሉበት ይካሄዳል።
  • ጨረታው የሚካሄደው በአቢሲንያ ባንክ .. ደሴ ዲስትሪክት 2 ፎቅ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ ነው።
  • የጨረታው አሸናፊ(ገዥ) ከሚገዛው ንብረት ጋር የተያያዙ ማናቸውም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎችን እንዲሁም ከስም ዝውውር ጋር የሚገናኙ ማናቸውም ወጭዎችን ይከፍላል።
  • ውዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሲሆን ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳ ደግሞ ወደ አሽናፊው ገዥው የሚተላለፍ ይሆናል።
  •  የጨረታው አሸናፊ ንብረቱ በሚገኝበት የከተማ አስተዳደር ዘንድ ቀርቦ ባሸነፈበት ንብረት ላይ የሚከፈሉ ክፍያዎችን ግብር እና ታክስ እንዲሁም ለመንግስት የሚከፈል 15% (አስራ አምስት በመቶ) የተጨማሪ እሴት ታክስ ካለ ይከፍላል።
  •  በባንኩ የብድር ፖሊሲና መመሪያ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ የጨረታው ከፍተኛ ዋጋ አቅራቢዎች ባንኩ ከፊል ብድር ሊሰጥ ይችላል።
  • ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ መጎብኘት የሚቻል ሲሆን ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 033-312-2223 በመደወል መጠየቅ ይቻላል።
  • ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብት አለው።

የተበዳሪው ስም

ከተበዳሪው የሚፈለግባቸው ቀሪ ዕዳ

የመያዣ ሰጭዎች ስም

የመያዣ ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የጨረታው መነሻ ዋጋ በብር

 

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ዓ.ም.

 

የምዝገባ ሰዓት

 

ጨረታው የሚከናወንበት ሰዓት

ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ

የመያዣ ንብረቱ አገልግሎት 

የቦታው ስፋት (በካ.ሜ)

የባለቤትነት መረጋገጫ ካርታ ቁጥር 

አቶ  ሳሙኤል ከበደ አበጋዝ

እስከ ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ ብቻ ያለው ተሰልቶ ብር 3,899,312.13

አቶ ታደሰ ሞላ ካሳ

አማራ ክልል ደሴ ከተማ አስተዳደር ፣መናፈሻ ክ/ከተማ ፣ቀበሌ 18/08 ል ስሙ ተቋም 

3,951,801.00

 

ሕዳር 11   ቀን 2018 ..

 

3:30-4:30

 

4:30-5:30

 

አቢሲንያ ባንክ አ. ደሴ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ፤ 2ኛ ፎቅ በሚገኝ የመሰብሰቢያ አዳራሽ 

ለመኖሪያ

 

299

 

A=14020

 

 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *