Your cart is currently empty!
አዲስ አበባ ሒልተን ኃ.የተ.የግማህበር ለሰራተኞች የሚሰጠውን የቀን ትራንስፖርት ህጋዊ ፍቃድ ላለውና ንግድ ፈቃድ ለ2018 የታደሰ ትራንስፖርት ሰጪ ድርጅት አወዳድሮ መስጠት ይፈልጋል
Reporter(Oct 19, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
አዲስ አበባ ሒልተን ኃ.የተ.የግማህበር ለሰራተኞች የሚሰጠውን የቀን ትራንስፖርት ህጋዊ ፍቃድ ላለውና ንግድ ፈቃድ ለ2018 የታደሰ ትራንስፖርት ሰጪ ድርጅት አወዳድሮ መስጠት ስለሚፈልግ በዚህ የስራ መስክ የተሰማራችሁ ድርጅቶች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ከሰኞ ጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም. እስከ አርብ ጥቅምት 14 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 3 ሰዓት – 6 ሰዓት ከአስተዳደር ክፍል የማይመለስ 300 ብር በመክፈል መውሰድ ይቻላል::
ተወዳዳሪዎች አገልግሎት የምትሰጡበትን ዋጋ ሞልታችሁ ከጥቅምት 17 ቀን 2018ዓ.ም. እስከ ጥቅምት19 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋት 3 ሰዓት – ቀኑ 10 ሰዓት ሰነዱ እንድታስገቡ::
ድርጅቱ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ መሆኑን እናሳውቃለን::
አዲስ አበባ ሒልተን