ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 19, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

በድጋሚ የወጣ የሂሳብ ምርመራ (የኦዲት) አገልግሎት ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የጨረታ ሰነድ ቁጥር 04/2018

የዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት ሂሣብን በተፈቀደላቸው ኦዲተሮች አዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።

በመሆኑም እያንዳንዱ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች በማሟላት በጨረታ ለመወዳደር ይችላል።

1. የድርጅቱን ሂሳብ በIFRS መሰረት ኦዲት ለማድረግ የሚያስችል የኦዲተርነት የሙያ ፈቃድ፣ የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር Tax Identification Number (TIN) ያለው።

2. የዘመኑን ግብር ከፍሎ የሙያ እና የንግድ ፈቃዱን ያሳደሰ።

3. ተጫራቾች ወቅታዊ ብቃታቸውንና ሙያዊ ስነ-ምግባራቸው በተመለከተ ከፈቃድ ሰጪው አካል ከዋናው ኦዲት መስሪያ ቤት እና ከኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ፤ ወይም ከሂሳብ አዋቂዎችና የግል ኦዲተሮች ማኅበር እንዲሁም ከዚህ በፊት ኦዲት ከደረጋቸው የልማት ድርጅቶች የመልካም ሥራ አፈጻጸም ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት።

4. የሂሣብ ምርመራው (ኦዲቱ) በባሕር ዳር ከተማ በሚገኘው የድርጅቱ ቅጥር ግቢ መሆኑን አውቆ የሚሳተፍ።

5. ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ባ/ዳር በሚገኘው ኮርፖሬሽናችን ወይም አዲስ አበባ በሚገኘው የድርጅታችን ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አመልድ ህንጻ ሰባተኛ ፎቅ ላይ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ሁለት መቶ ብር/ከፍሎ ከድርጅቱ በመግዛት መጫረት ይቻላል።

6. ተጫራቾች ጠቅላላ ዋጋቸውን (ታክሱን ጨምሮ) በጨረታ መመሪያው መሰረት በመሙላት የቴክኒክ መወዳደሪያ ሰነድ” ፣ “የዋጋ መወዳደሪያ ሰነድ” እና “የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /Bid Bond/ ማስያዣን በ2 የተለያዩ ፖስታዎች በማሸግ የጨረታ ማስከበሪያው ሰነድ የታሸገበትን ፖስታ የቴክኒካል መወዳደሪያው ሰነድ ካለበት ፖስታ ውስጥ አስገብቶ በማሸግ በተራ ቁጥር 5 በተገለጸው የሥራ ቀናት ውስጥ ባሕር ዳር በሚገኘው የኮርፖሬሽኑ ቢሮ ቁጥር 107 ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ከላይ በተገለጸው መሰረት ሰነዶቹን አዘጋጅቶና አሽጎ ያልቀረበ ተወዳዳሪ ወይም ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።

7. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ስዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ8፡30 ስዓት በኮርፖሬሽኑ ቢሮ ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 107 ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው ባሉበት ጨረታው ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡30 ሰዓት ይከፈታል።

8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር፡- 058-321-7806/09276055/ ባሕር ዳር

ዘመን ኮንስትራክሽን ኮርፖሬሽን


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *